Saturday, 23 December 2017 10:53

“በመንገደኛ” መጽሐፍ ላይ ነገ ውይይት ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

ሚዩዚክ ሜይዴይ፤ በዮርዳኖስ አልማዝ ሰይፉ በተፃፈው “መንገደኛ” በተሰኘ የጉዞ ማስታወሻ መፅሐፍ ላይ በነገው ዕለት ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ፣በብሔራዊ ቤተመፃህፍትና ቤተመዛግብት ኤጀንሲ (ወመዘክር) አዳራሽ ውይይት ያካሂዳል፡፡
ለውይይቱ መነሻ ሃሳብ የሚያቀርበው የ”አዲስ አድማስ” ዋና አዘጋጅ፣ ገጣሚ ነቢይ መኮንን ሲሆን ፍላጎቱ ያላቸው ወገኖች በፕሮግራሙ ላይ እንዲታደሙ አዘጋጁ ጋብዟል፡፡ 

Read 1390 times