Tuesday, 02 January 2018 10:18

“ቅኔ- ዘፍልሱፍ” ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በደራሲ ካሳሁን አለሙ የተሰናዳው “ቅኔ-ዘፍልሱፍ” የተሰኘ መፅሐፍ ገበያ ላይ ዋለ። መፅሐፉ የፍልስፍናን ቅኔነት የሚሞግት የመጀመሪያው መፅሀፍ ሊሆን እንደሚችልና በዚህ እይታ የተፃፈ ሌላ መፅሀፍ ፈልገው ማጣታቸውን በመግቢያቸው ላይ ያሰፈሩት ፀሃፊው፤ አንባቢያን በእርጋታና በተመስጦ የሚያነቡት እንጂ በ“ላፍ ላፍ” ሊረዱት እንደማይችሉ አሳስበዋል፡፡
መጀመሪያ ላይ መፅሀፉ የፍልስፍናን ቅኔነትና የቅኔን ፍልስፍናነት አጣምሮ ሊዘጋጅ ታስቦ የነበረ ቢሆንም በኋላ ላይ ሁለቱም ሀሳቦች ራሳቸውን ችለው በመፅሀፍ እንዲቀርቡ መወሰናቸውን ፀሐፊው ጠቁመዋል፡፡ በዚህም መሰረት የፍልስፍና ቅኔነት የሚለውን አስቀድመው ሌላውን በቀጣይ ለማሳተም ማሰባቸውን ገልፀዋል፡፡
በአራት ምዕራፎች ተከፍሎ በ272 ገፆች የተመጠነው መፅሐፉ፤ በ79 ብር ከ99 ሳንቲም እተሸጠ መሆኑ ታውቋል፡፡ ደራሲው ከዚህ ቀደም “ህልዎተ እግዚአብሄር”፣ “መሰረታዊ ሎጂክና ሕፀዕ” እና “ብዕረ ንዋይ” የተሰኙ መፅሐፍትን ለንባብ ማብቃታቸው ይታወቃል፡፡

Read 1640 times