Tuesday, 02 January 2018 10:15

“ፍቅርና ሽንቁር” የግጥም መፅሀፍ ነገ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(15 votes)

የደራሲና ገጣሚ ዳንኤል ስዩም መንገሻ “ፍቅርና ሽንቁር” የተሰኘ የግጥም መፅሀፍ ነገ ከ3፡30 ጀምሮ በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን አዳራሽ ይመረቃል፡፡ መፅሀፉ በማህበራዊ፣ በፍቅርና በፍልስፍና ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ ከ45 በላይ ግጥሞችን ያካተተ ሲሆን በ84 ገፆች ተቀንብቦ፣ በ40 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡
በምርቃቱ ስነ-ስርዓቱ ላይ የፍልስፍና ምሁሩ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ በመፅሀፉ ላይ ደሰሳ የሚያቀርቡ ሲሆን ገጣሚያኑ ሙሉቀን ሰለሞን፣ ናትናኤል ጌቱ፣ ሰይፉ ወርቁና በላይ በቀለ ወያ ግጥም እንደሚያነቡ ለማወቅ ተችሏል፡፡ መድረኩ በእውቁ ገጣሚ ሰለሞን ሳህለ ይመራል ተብሏል፡፡

Read 4056 times