Print this page
Tuesday, 02 January 2018 10:20

የገና በዓል ልዩ የመፅሐፍት አውደ ርዕይ ተከፈተ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(4 votes)

 ከ10 በላይ የመፅሐፍት መደብሮች ያዘጋጁት የገና በዓል ልዩ የመፅሀፍት አውደ ርዕይ ትላንት በብሄራዊ ቴአትር ጋለሪ አዳራሽ ተከፈተ፡፡ እስከ ገና ዋዜማ ለተከታታይ ዘጠኝ ቀናት የሚቆየው አውደ ርዕዩ፤ በዓሉ የስጦታ ካርዶች መለዋወጫና ፍቅር መገላለጫ እንደመሆኑ ሰዎች የህይወት ስንቅ የሆኑ መፅሀፍትን ለወዳጅ ዘመድ በስጦታ እንዲያበረክቱ እድል ይከፍትላቸዋል ተብሏል፡፡
“ከአስተዋይ ሰው ጀርባ መፅሀፍት አሉ” በሚል መርህ በተዘጋጀው በዚህ አውደ ርዕይ ላይ መንፈሳዊና ዓለማዊ መፅሐፍትን ጨምሮ ለተማሪዎችና ለመምህራን አጋዥ የሆኑ፣ በርካታ አይነት መፅሐፍት የሚቀርቡ ሲሆን ከ20 እስከ 50 በመቶ የዋጋ ቅናሽ እንደሚኖራቸው ተገልጿል።
የመፃህፍት አውደ ርዕይ አዘጋጆች፡- እነሆ መፅሀፍት፣ ኤዞፕ መፃህፍት፣ ዮናስ መፃህፍት፣ የዕውቀት በር መፃህፍት፣ ፍሬው መፃህፍት፣ ድጋፍዬ መፃህፍት፣ ቤሪያ፣ መላኩ፣ አቡጊዳና መጋቢ መፅሀፍት መደብሮች እንደሆኑ ታውቋል፡፡

Read 3731 times