Saturday, 06 January 2018 13:04

“ያለፍኩበት” መፅሐፍ ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 የዶ/ር ፍስሀ አስፋውን የህይወት ታሪክ የሚያስቃኘውና በራሳቸው በዶ/ሩ የተፃፈው “ያለፍኩበት” መፅሐፍ ዛሬ ከረፋዱ 5፡00 ጀምሮ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ይመረቃል፡፡
የፎቶ ምስሎችን ጨምሮ በ267 ገፆች የቀነበበውና በ81 ብር ከ50 ሳንቲም ለገበያ የቀረበው መፅሐፉ ዶ/ር ፍስሀ ከልጅነታቸው እስከ ውትድርና ህይወታቸውና በአካዳሚክ ትምህርት አሁን የደረሱበትን የህይወት ጉዞ ያስቃኛል፡፡
በምርቃት ሥነ - ሥርዓቱ ላይ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ለውይይት የመነሻ ሀሳብ የሚያቀርቡ ሲሆን፣ ሞላ ዘገዬ፣ ኮ/ል ፍስሀ ደስታ፣ ዶ/ር ሃይሉ አርአያ፣ ሻምበል ፍቅረስላሴ ወግደረስና ሻለቃ መላኩ ተፈራ ተገኝተው በመፅሀፉ ላይ አስተያየት እንደሚሰጡ ተገልጿል፡፡

Read 1384 times