Print this page
Saturday, 06 January 2018 13:07

ሞርጋን ሄሪቴጅ ዛሬ በኤቪ ክለብ ይጫወታሉ

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

 በ2016 እ.ኤ.አ በምርጥ የሬጌ አልበም የግራሚ ተሸላሚ የሆኑት ሞርጋን ሄሪቴጅ፤ዛሬ በገና ዋዜማ ፍሬንድሺፕ ህንጻ ሥር በሚገኘው ኤቪ ክለብ ሙዚቃቸውን ያቀርባሉ፡፡ የሬጌ ሙዚቃ ‹ንጉሣዊ› ቤተሰብ የሚባሉት ሞርጋን ሄሪቴጅ፣በኢትዮጵያ የሙዚቃ ስራቸውን ሲያቀርቡ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን በኤቪ ክለብ የሚያቀርቡትን ልዩ የሙዚቃ ድግስ ያዘጋጁት ኤችአይኤም ኢንተርናሽናልና ሃበሻ ዊክሊ ፕሮሞሽን ከሄኒከን ቢራ ጋር በመተባበር ነው፡፡ ኢትዮጵያውያኑ የሬጌ ሙዚቀኞች ራስ ጃኒና ዮሐናም በምሽቱ ይጫወታሉ ተብሏል፡፡ የዋዜማ መግቢያው በመደበኛ 400 ብር፣ በቪአይፒ ደግሞ 500 ብር እንደሆነ ታውቋል፡፡
በ2015 ለገበያ በበቃው ‹‹ስትሪክትሊ ሩትስ›› በተባለው አልበማቸው፣በዓመቱ በተካሄደው 58ኛው የግራሚ ሽልማት እጩ ከሆኑ በኋላ ሞርጋን ሄሪቴጅ፣ ወደ አዲስ አበባ መጥተው፣ በኤች2ኦ ክለብ የሙዚቃ ሥራቸውን ማቅረባቸው የሚታወስ ነው፡፡ ከአዲስ አበባ ዝግጅታቸው በኋላም በአሜሪካ የግራሚ ሽልማታቸውን በምርጥ ሬጌ አልበም አሸንፈው ተቀብለዋል፡፡ በ2017 ባሳተሙት “Avrakedabra” የተሰኘ አልበማቸውም በግራሚ ሽልማት፣ የምርጥ የሬጌ አልበም ዘርፍ እጩ ለመሆን በቅተዋል፡፡
ሞርጋን ሄሪቴጅ እስከ 2017 ዓ.ም በመላው ዓለም ከ309 በላይ ኮንሰርቶችን ያቀረቡ ሲሆን በተገባደደው የፈረንጆች ዓመት በተለያዩ የዓለም አገራት 10 ኮንሰርቶችን እንደሰሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከኢትዮጵያ እንደተመለሱ ከ1 ወር በኋላ በአውሮፓ የተለያዩ አገራት 10 ኮንሰርቶችን እንደሚያቀርቡም ይጠበቃል፡፡

Read 1827 times