Saturday, 06 January 2018 13:11

የዘነበ ወላ “መልህቅ” መፅሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(8 votes)

    አብዛኛውን የህይወቱን ክፍል በባህር ላይ ያሳለፈው መርከበኛ ዘነበ ወላ “መልህቅ” የተሰኘ መፅሐፍ ሰሞኑን ለንባብ በቃ፡፡
መፅሐፉ በዋናነት ፀሃፊው በባህር ላይ እና በአስመራ ያሳለፈውን የህይወት ጉዞና ገጠመኝ የሚያስቃኝ ነው ተብሏል፡፡ ዘነበም “በዚህ ጥራዝ ውስጥ የምታገኙት አስመራ በነበርኩበት ጊዜ ህይወት በሰራ አካላቴ የከተበችውን ነው” ሲል በመግቢያው አስፍሯል፡፡
በ58 ክፍሎች ተከፋፍሎ በ448 ገፆች የተቀነበበው መፅሐፉ፤ ለአገር ውስጥ በ150 ብር እና ለውጭ አገር በ25 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡ ደራሲው ከዚህ ቀደም “ህይወት በባህር ውስጥ”፣ “ማስታወሻ” እና “ልጅነት” የተሰኙ መፅሐፍትን ለንባብ ማብቃቱ ይታወሳል፡፡

Read 6032 times