Saturday, 21 April 2012 16:35

“የsemen, sperm ,testosterone …መጠን ...ጥራትና ብቃት ...”

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(17 votes)

....አንድ ወንድ ወሲባዊ ግንኙነት በሚያደርግበት ጊዜ ከ2-6 ሚሊሊትር የሚደርስ መጠን ያለውና በእያንዳንዱ ሚሊሊትር እስከ 20/ሚሊዮን የሚደርስ የወንድ  የዘርፍሬ እንዲለቅ የሚጠበቅ ሲሆን ከነዚህም ግማሽ ያህሉ ከተለቀቁ ከአንድ እስከ ሁለት እና ሶስት ሰአት ድረስ ተንቀሳቃሾች ናቸው፡፡ ወደ 60  ና ከዚያ በላይ የሚሆኑት ትክክለኛ ተፈጥሮአዊ ቅርጽና ገጽታ ያላቸው ናቸው፡፡ ነገር ግን ከ10 እስከ 15 ሚሊዮን የሚሆኑት የዘር ፍሬዎች ወንድ ልጅን ልጅ ለማግኘት ያስችሉታል.....

ወንዶች ልጅ እንዲኖራቸው ለማስቻል ሁሉም የስነተዋልዶ አካላት ማለትም ውስጣዊ ...በሳይንሳዊው አጠራር semen, sperm ,testosterone የተባሉት እና ውጫዊ አካል ጤነኛ ሆኖ መገኘት ግድ ነው፡፡ እነዚህ የወንዶች የስነተዋልዶ አካላት በምን ምክንያት ጉዳት ይደርስባቸዋል የሚለውን ዝርዝር ሁኔታ ለጊዜው ተወት እናድርግና በአኑዋኑዋር ሁኔታ የሚደርሰውን የጤና መስተጉዋጎል ለአንባቢዎች እንላለን፡፡ ለዚህ እትም ምንጭ ያደረግነው የተለያዩ መረጃዎችን ሲሆን ባብዛኛው ግን http://www.livestrong.com  የተሰኘውን ድህረ ገጽ ነው፡፡ በዚህ መረጃ ወንዶች በአመጋገብ እና በአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንዲሁም በተለያዩ ባህርይዎች ሳቢያ እና በአየር ጸባይ ምክንያትም ጭምር ዘር አልባ ሊሆኑ እንደሚችሉ የሚያሳይ ሰፋ ያለ መረጃ ለንባብ ቀርቦአል፡፡

የወንዶች ዘር አልባነት መንስኤ ምንድነው የሚለውን ሙሉ በሙሉ በእርግጠ ኝነት መናገር ባይቻልም አንዳንድ ምክንያቶን ግን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ፐብ ሜድ የተባለው መረጃ ባስነበበው መሰረት ዘር ለማግኘት ምርመራ ከሚያደርጉ 10  ሰዎች ግማሽ ያህሉ ወንዶች መሆናቸውን እና ከተደረገውም ምርመራ ወደ 25  የሚሆነው የወንዶች semen የተሰኘው ፈሳሽ ጤንነቱ የተጉዋደለ መሆኑ ተረጋግጦአል፡፡

እንደውጭው አቆጣጠር ከ1930 ዎቹ አመተ ምህረት ጀምሮ በሚደረጉት የጤና ምርመራዎች እንደሚታየው ወንዶች የሚኖራቸው የእስፐርም መጠን ቀንሶ እንደሚታይ ኼልዝ ኮሚዩኒቲስ የተባለው ድህረገጽ ያስነብባል፡፡  በእርግጥም ይላል መረጃው ዘመኑ እየሰለጠነና እየተራቀቀ በመጣ ቁጥር የተለያዩ ለውጦችም አብረው መመዝገባቸው አልቀ ረም፡፡ በመሆኑም ከተጠቀሰው አመተምህረት ወዲህ የአካባቢ ሁኔታ መለወጥ ...የአየር እና የመሳሰሉት መመረዝ ...ፀረተባይ የመሳሰሉትና አንዳንድ የአኑዋኑዋር ሁኔታዎች መሻሻል ተዳምሮ የሰዎችን አካላዊ እንቅስቃሴ የሚጠይቅ ሳይሆን ከበቂ በላ እረፍት በማድረግና በመቀመጥ የተተካ ስለሆነ ለወንዶች ዘር አልባነት እንደ አንድ መንስኤ ይወሰዳል ይላል ያኘነው መረጃ፡፡

ከላይ ያነበባችሁት በታሪክ መልክ የተጠቀሰውን ሲሆን የወንዶችን ዘር አልባነት በሚመለከት በምርምር ከተገኙት ምክንያቶች አመጋገብ አንዱ ነው፡፡ ምግብን አመጣጥኖ እና ጠቀሜታ ያላቸውን መውሰድ የወንዶች የዘር ፈሳሽ እስፐርም እንዳይጎዳ ይረዳል፡፡ በ2009 እና በ2010  እንደውጭው አቆጣጠር ዘር ማግኘትና መካንነት በሚል የወጣ አንድ ጆርናል እንደሚጠቁመው በሰውነት ውስጥ ሊከሰቱ የሚችሉትን መርዛማ ነገሮች የሚያስወግዱትን ምግቦች ዝቅ አድርገው የሚመገቡና በተቃራኒው ደግሞ እንደ ስጋ ወተት የመሳሰሉ ምግቦችን በተደጋጋሚ የሚወስዱ የዘር ፈሳሻቸው መጠንና ፍጥነት ደካማ እንደሚሆን ይገልጻል፡፡ የማዮ ክሊኒክ ባለሙያዎች እንደሚገልጹት ቫይታሚን ሲ እና ዚንክ የመሳሰሉት ንጥረ ነገሮች ያሉባቸውን ምግቦች የሚወስዱ ወንዶች ግን ልጅ ለማስወለድ የሚያስችል አቅም አላቸው፡፡ በእርግጥ ይህ ሲባል ሁሉም ልብ ሊለው የሚ ገባው ተመጣጣኝ የሆነ ምግብ መውሰድ ማለት ክብደትን መጨመር ወይንም መቀነስ የሚለውን እንዳያስከትል መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ሰውነት ከልክ በላይ ከወፈረ ወይንም ከቀጠነ ለወንዶችም ይሁን ለሴቶች የሆርሞን መዛባትን ሊያስከትል የሚችል ችግር ስለሆነ ልጅ የማግኘት እድልን ሊያጨናግፍ ይችላል፡፡

የወንዶችን ዘር ማግኘት ከአመጋገብ ጋር ስናያይዝ የትኛው ምግብ ይጠቅማል ? የትኛው  አይጠቅምም የሚለውን በመጠኑ እናስነብብ ፡፡

Calories ካሎሪ

ካሎሪ በብዛት የሚገኝባቸው ምግቦች በሰውነት ላይ ክብደት እና ስብን የማከማቸት ኃይላቸው ከፍተኛ ነው፡፡ ከዚህም በላይ በካሎሪ የዳበሩ ምግቦችን ማብዛት ዘር አልባ ለመሆንም መንገድ ሊከፍት ይችላል ይላሉ ተመራማሪዎቹ፡፡ የዚህም ምክንያቱ ስስትሮን የተባለው ሆርሞን እና እስፐርም እንዲሁም ተያያዥ የሆኑ የስነተዋልዶ አካላት መጠንና ጥራት እንዲሁም ብቃታቸውን ስለሚቀንስ ነው፡፡

Acrylamides

ከላይ በተጠቀሰው አርእስት ስር ከተቀመጡት የምግብ አይነቶች የድንች ጥብስ ይገኝበታል፡፡ በድንች ውስጥ በተፈጥሮ የሚገኘው ስኩዋር እና አሚኖ አሲድ ድንቹ በሚጠበስበት ወይንም ጊዜ ሙቀት ስለሚያገኘው ለካንሰር የሚያጋልጠውን መርዛማ ነገር ሊፈጥር ይችላል፡፡ ይህ ምግብ የወንዶችን የዘር ፈሳሽ እስፐርም ስለሚቀንስ ለዘር አልባነትም ሊዳርግ እንደሚችል በቻይና የሚገኝ ሻንኪ የሚባል የግብርና ዩኒቨርሲቲ ይፋ አድርጎአል፡፡

Animal products የእንስሳት ተዋጽኦ

ሀምበርግር ...ሆት ዶግ ...ቺዝ እና በተለያዩ ካፌዎች በወተት የሚሰሩ ጁስ መጠጦች እና ተመሳሳይ ምግቦችን መመገብ የተለመደና ለመመገብም ቀላልና ምቹ መንገዶች እንዲሁም ምርጫዎች ተደርገው ሲወሰዱ ይታያሉ፡፡ እነዚህ ምግቦች ግን ከፍተኛ መጠን ያለው ካሎሪን የያዙ ሲሆን የስብና የሶዲየም መጠንን በከፍተኛ ሁኔታ በሰውነት ውስጥ የሚጨምሩ ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ዘር የማግኘትን እድል አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ናቸው፡፡ ይልቁንም ወንዶች የፍራፍሬ እና የአትክልት አመጋገባቸውን ቢያሻሽሉ የዘር ፈሳሻቸው መጠን ጥራትና ብቃት ስለሚጨምር ያለዘር ከመቅረት ይድናሉ ይላል በ2009 የወጣው Fertility & Sterility ወወላድነትና መንንት የተሰኘው ጥናት፡፡

ወንዶች ያለዘር የሚቀሩባቸው አንዳንድ ምክንያቶች፡-

በዘር መተላለፍ፡-

ዘር አልባነት ከቤተሰብ በዘር ሀረግ ሊተላለፍ እንደሚችል ጥናቶች ያረጋገጡ ሲሆን በተለይም የወንዱ Y የተሰኘው chromosome ሲዛባ ወንዱ ልጅ ለማስረገዝ አይችልም፡፡ የዚህ አይነት ችግር ያለው ሰው እንደእድል ሆኖ ልጅ ማስወለድ ቢችልም እንኩዋን የተወለደወ ወንድ ልጅ ከሆነ በአባትየው ላይ የደረሰው የጤና ችግር ለልጁ ሊተላለፍ ይችላል፡፡

የሆርሞን መዛባት፡-

ወንዶች የሆርሞን መዛባት ሲያጋጥማቸው ዘር አልባ ይሆናሉ ፡፡ ሁኔታው አንዳንድ ጊዜ የካንሰር ችግር የሚያመጣ ሲሆን ካንሰርን ለመከላከል ሲባል በሚደረግ የህክምና ክትትልም ሳቢያ ዘር አልባ የመሆን እድል ሊከሰት ይችላል፡፡

ተፈጥሮአዊ፡-

አንዳንድ ወንዶች ሲፈጠሩ ከብልታቸው semen ሲመን የተሰኘውን ፈሳሽ በግንኙነት ጊዜ በትክክለኛው መንገድ ለማስኬድ የሚያስችሉ ቱቦዎች ላይፈጠሩላቸው ይችላል፡፡ ይህ መስመር በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳም ጉዳት የደረሰበት ከሆነ የዘር ፈሳሽን በትክክለኛው ፍጥነትና መጠን ወደሴቷ ብልት ማስኬድ ስለማይችል ልጅ ሊፈጠር አይችልም፡፡

ከሕመም ጋር በተያያዘ፡-

ወንዶች በአንዳንድ ሕመም ምክንያት ለምሳሌ እንደ ካንሰር ፣የስኩዋር ፣የሳንባ በሽታ የመሳሰሉት ከገጠሙዋቸው የእስፐርም መጠናቸው ከሚፈለገው መጠን በታች ዝቅ ያለ ሊሆን ይችላል፡፡

አካባቢያዊ ሁኔታዎች፡-

ከፍተኛ ሙቀት ላለበት ቦታ መጋለጥ ዘር አልባነትን ሊያስከትል ይችላል፡፡ የማይክሮ ዌቭ ጨረር ወይንም ፀረተባይ መድሀኒትን በመርጨት ስራ ላይ መሰማራት ለወንዶች ዘር ላለማግኘት ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡

ባህርይ፡-

አንዳንድ ወንዶች በባህሪያቸው መጠጥ የሚያዘወትሩ ፣ሱስ አስያዥ እጾችን የሚጠ ቀሙ፣ ሲጋራ የሚያጨሱ ከሆኑ የዘር ፈሳሽ ጥራትን ሊቀንስ ይችላል፡፡

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፡-

እስፖርት መስራት ለማንኛውም ሰው ጥሩ እንደሆነ ይመከራል፡፡ ነገር ግን የሚሰራው እስፖርት ጥንቃቄ የተመላበት ካልሆነ የወንድ የዘር ፈሳሽን ሊጎዳ ይችላል፡፡

እድሜ፡-

እድሜ የወንድ የዘር ፈሳሽን መጠንና ጥራት ሊቀንስ ይችላል፡፡

ካንሰር እና ካንሰርን ለመከላከል የሚደረግ ሕክምና፡-

በካንሰር በሽታ መያዝና አንዳንድ ካንሰርን ለመከላከል ሲባል የሚደረጉ ሕክምናዎች የወንድን ዘር የማግኘት እድልን በጊዜያዊ ወይንም በዘለቄታው ሁኔታ ሊያስተጉዋጉል ይችላል፡፡

 

 

Read 25681 times Last modified on Saturday, 21 April 2012 16:49