Saturday, 13 January 2018 15:36

የብላቴን ጌታ ህሩይ ወ/ሥላሴ የሥነ ጥበብ ማዕከል 21ኛ መድረኩን ዛሬ ያካሂዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

  በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ውስጥ የሚገኘው የብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደ ሥላሴ የስነ ጥበብ ማዕከል፣ ዛሬ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ 21ኛ መድረኩን ያካሂዳል፡፡
የዚህ መድረክ ትኩረት በቅርቡ ለአራት ወራት ውሎና አዳሩን በማዕከሉ በማድረግ (Art Residensy) 27 ስዕሎችን ሰርቶ፣ በግቢው “አብዮት እንደበረከት” በሚል ስያሜ የስዕል አውደ ርዕይ በከፈተው የቸርነት ወ/ገብርኤል ሥራዎች ላይ እንደሚሆን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ሰዓሊው ከስዕሎቹ በተጨማሪ ተወዳጅ ግጥሞቹን ለታዳሚ እንደሚያቀርብም ለማወቅ ተችሏል፡፡
ለስዕል ሥራዎቹ ውይይት የመነሻ ሀሳብ የሚያቀርቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአለ የስነ-ጥበብ ዲዛይን ት/ቤት ዳይሬክተር፣ ሰዓሊ አገኘሁ አዳነ ሲሆን ፍላጎቱ ያለው ሁሉ በውይይቱ ላይ እንዲሳተፍ የማዕከሉ ኃላፊ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ጋብዟል፡፡

Read 1135 times