Saturday, 13 January 2018 15:40

የአለማየሁ ገላጋይ “በፍቅር ስም” ነገ ውይይት ይደረግበታል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

  እናት የማስታወቂያ ድርጅት ከጎተ ኢንስቲትዩትና ከብሄራዊ ቤተ መፃህፍትና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ ጋር በመተባበር በደራሲና ሀያሲ ዓለማየሁ ገላጋይ “በፍቅር ስም” የተሰኘ መፅሐፍ ላይ ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በወመዘክር ውይይት ያካሂዳል፡፡
ለውይይት የመነሻ ሀሳብ የሚያቀርቡት የሥነፅሁፍ ባለሙያው ቴዎድሮስ አጥላው ሲሆኑ ፍላጎት ያለው በውይይቱ ላይ እንዲሳተፍ አዘጋጁ  ጋብዟል፡፡

Read 2668 times