Saturday, 13 January 2018 15:41

የአለቤ ሾው 13ኛ ሙት ዓመት በጥበባዊ ዝግጅቶች ይከበራል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

  ከ13 ዓመት በፊት በመኪና አደጋ ህይወቱን ያጣውንና “የድሆች አባት” በሚል የሚታወቀውን  የአርቲስት አለባቸው ተካ (አለቤ ሾው)  ሙት ዓመት፣ “አለቤ 13 ዓመት በሰዎች ልብ ውስጥ” በሚል የፊታችን ሰኞ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ እንደሚከበር አዘጋጁ፣ አብሀበን የማስታወቂያ ድርጅት አስታውቋል፡፡
በዚህ ፕሮግራም ላይ የ30 ደቂቃ ርዝመት ያለውና አለቤ ሲሰራቸው የነበሩትን ስራዎች የሚያስታውስ ዘጋቢ ፊልም፣ ደግነትን የሚያወሱ ሙዚቃዎች፣ ግጥሞችና ሌሎች የኪነ ጥበብ ዝግጅቶች እንደሚቀርቡ አዘጋጁ ጠቁሟል፡፡ በተጨማሪም አቋቁሞ በካምፕ ያኖራቸው ከነበሩ 70 ያህል የሴት እግር ኳስ ቡድን አባላት መካከል ጥቂቶች፣ አለቤ አስተምሯቸው ለቁምነገር የበቁ አርቲስቶችና ግለሰቦች ስለ አለቤ ምስክርነት እንደሚሰጡ የተገለጸ ሲሆን መድረኩም በአርቲስት ጥላሁን እልፍነህ እንደሚመራ ታውቋል።  የአለቤን 13ኛ ሙት ዓመት አስመልክቶ በተዘጋጀው መፅሄት ላይ በመኪና አደጋ ያጣናቸው አርቲስት ሰብለ ተፈራ (እማማ ጨቤ) እና ድምፃዊ ሀ/ሚካኤል ደምሴ አብረው እንደሚዘከሩም ተጠቁሟል፡፡  

Read 2848 times