Saturday, 20 January 2018 13:12

“ሙሉ ጤናን ፍለጋ” መፅሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በህክምና ባለሙያው ዶ/ር ይሁኔ አየለ የተሰናዳውና ራስንና አስተሳሰብን በመለወጥ ጤንነት ጠብቆ ለመኖር የሚያስችሉ መሰረታዊ ዕውቀቶችን ያስጨብጣል የተባለው “ሙሉ ጤናን ፍለጋ ቁልፉ የት ይሆን” የተሰኘ መፅሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ መጽሐፉ በተለያዩ ባዕድ አስተሳሰቦች የተነሳ ወደ ትክክለኛ ህክምና ባለመሄድ ብዙዎች መኖር ሲችሉ ህይወታቸውን እያጡ መሆኑን ግንዛቤ ለማስጨበጥ ታስቦ የተዘጋጀ ነው ተብሏል፡፡  
ደራሲው የመጽሐፉን መታሰቢያነት በግንዛቤ እጥረት በሽታቸውን በቡዳ  በዛር፣ በመናፍስት፣ በተፈጥሮ ክስተትና በፈጣሪ ቁጣ በማመካኘት ትክክለኛ ህክምና ሳያገኙ ህይወታቸውን ላጡ፣ ቡዳ ተብለው ለተገደሉ፣ ለተደበደቡ፣ ለተሰደዱ፣ “አንተ ጎደሎ” ተብለው ከማህበረሰቡ ተገልለው በስነ ልቦና ስቃይ ለሚንገላቱ ወገኖች ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡ በ11 ምዕራፎች ተከፋፍሎ፣ በ334 ገፆች የተቀነበበው መፅሐፉ፤ ለአገር ውስጥ በ120 ብርና ለውጭ አገራት በ20 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 3382 times