Saturday, 20 January 2018 13:13

“ርእየ ዮሐንስ” መፅሐፍ ተሻሽሎ በድጋሚ ታተመ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(6 votes)

 ቀደም ሲል በዲያቆን ዳንኤል ክብረት ተዘጋጅቶ ለንባብ የበቃውና  ለረጅም ጊዜያት ከገበያ ጠፍቶ እንደቆየ የተነገረለት “ርእየ ዮሐንስ” የተሰኘው መፅሐፍ በድጋሚ ተሻሽሎ ለገበያ ቀረበ፡፡
መፅሐፉ በሀዲስ ኪዳን ብቸኛው የትንቢት መፅሐፍ ሲሆን በምሳሌዎች፣ ምልክቶችና ትንቢቶች የተሞላ በመሆኑ በብዛት እንደማይተረጎም በመግቢያቸው የጠቆሙት ዲያቆን ዳንኤል፤“ርእየ ዮሐንስ” እነዚህን ክፍተቶች ለመሙላት የአባቶች ምስጢራትንና ትርጓሜዎችን በማካተት ዳብሮና ተሻሽሎ በድጋሚ መታተሙን አመልከተዋል፡፡ በ566 ገፆች የተቀነበበው መፅሀፉ፤ የመሸጫ ዋጋው 460 ብር መሆኑ ታውቋል፡፡

Read 3804 times