በዶ/ር አለማየሁ አረዳ የተፃፈው “ምሁሩ” የተሰኘው መፅሐፍ ከነገ ወዲያ ሰኞ ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ በራስ ሆቴል በኪነ ጥበባዊ ዝግጅት እንደሚመረቅ ተገለፀ፡፡
መፅሐፉ በዶ/ር ዳኛቸው አሰፋና በሰርፀፍሬ ስብሃት ዳሰሳ እንደሚደረግበት ታውቋል፡፡ በተጨማሪም ገጣሚያኑ፡- ነቢይ መኮንን፣ ፍሬዘር አድማሱ፣ ሰለሞን ሳህለ፣ መርዕድ ተስፋዬ፣ ሰይፉ ወርቁ፣ ረድኤት ተረፈና ምስራቅ ተረፈ በፒስትርዮ ቫዮሊን ግሩፕ ታጅበው ስራቸውን ያቀርባሉ ተብሏል፡፡
Saturday, 20 January 2018 13:14
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና