Saturday, 27 January 2018 11:34

አምስት የህፃናት መጻህፍት ለገበያ ቀረቡ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

የህፃናት መፅሐፍትን ለንባብ በማብቃት የሚታወቀው “ምንጭ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር” ከብዕር ማተሚያ ቤት” ጋር በመተባበር፣ አምስት የህፃናት መፅሐፍትን ሰሞኑን ለንባብ አብቅቷል፡፡
“እምነት ጠፋ፣” “ተገረምኩ”፣ “ክራሬን ሳምኳት”፣ “ለወገን ደራሽ” እና “ዛፎቹ ተገነደሱ” የተሰኙት የህፃናት መፃህፍቱ፤ተረቶችን በምስል አስደግፈው የያዙ ሲሆን ሁሉም በተረቶቹ መጨረሻ ድህረ-ጥያቄዎች  ተዘጋጅቶላቸዋል፡፡ ከ8- 16 በሚሆኑ ገጾች የተሰናዱት የህጻናት መጻህፍቱ፤ከ28 ብር - 32 ብር በሆነ ዋጋ ለገበያ ቀርበዋል፡፡


Read 3791 times