Saturday, 27 January 2018 11:39

“ድርና ማግ” የኪነ ጥበብ ምሽት ሐሙስ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 ሁለተኛው ዙር “ድርና ማግ” የኪነ ጥበብ ምሽት፣ የፊታችን ሐሙስ፣ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ  መገናኛ በሚገኘው አፋረንሲስ ኢንተርናሽናል ሆቴል ይካሄዳል፡፡
መድረኩን የምታጋፍረው የፕሮግራሙ አማካሪ አርቲስት አዜብ ወርቁ ስትሆን ሰዓሊና ቀራጺ በቀለ መኮንን፣ ደራሲና ሀያሲ ዓለማየሁ ገላጋይ፣ ገጣሚ ታገል ሰይፉ፣ አርቲስት ሰለሞን ቦጋለና ዶ/ር መንበረ አክሊሉ (ከሳንፍራንሲስኮ በግብዣ) የጥበብ ሥራቸውን ለታዳሚው እንደሚያቀርቡ ታውቋል፡፡ የኪነ ጥበብ ምሽቱ  በመሶብ የባህል ባንድ እንደሚታጀብ አዘጋጆቹ ተናግረዋል፡፡   

Read 3229 times