Saturday, 27 January 2018 12:48

መሰናበቻ ለሰለሞን ደሬሳ

Written by  ከተስፋዬ ገሠሠ (ተባ ፕሮፌሰር)
Rate this item
(0 votes)

 የሰለሞን ፈር ቀዳጅ ስነ ግጥም አፃፃፍ ዘዬ በመከተል “እንደ ሰለሞን ደሬሳ” የምትል ለፈገግታ ያህል ትንሽ ግጥም በ1993 ዓ.ም ጽፌ ነበር “በእንግሊዝኛ” “ፓሮዲ”
ድሃ በህልሙ
ቅቤ ባይጠጣ
ሲፎክት ይደር
ሲፎክታታ!

ጌታ በውኑ
ቅቤ ባይጠጣ
በሕልሙ ይደር
ሲደርድራታ!

ኧረ! መገለጢጥ
ቁብ- ቂጥ- ቂጥጥ
ዙጵ- ዚጵ- ዚጲጵ
     ጲጵ!

መኪና ነኝ!
ምን ትሆኑ!
ኮንኮላታ-ታ!
ወሎታታ-ታ!
መጨረሽታ-ታ!
ፓሮዲ በጽሁፍ ወይም በሙዚቃ ሆን ተብሎ አንድ የታዋቂ ደራሲን ዘዬ በመገልበጥ (ኮፒ በማድረግ) ለማሳቅ የሚፃፍ ነው፡፡ የማሾፍም ዓይነት፡፡ ሰሎሞን አሁንም በሕልፈትህ ላሹፍብህ፡፡
ሞትኩላችሁ!
ምን ትሆኑ!
አመድ ሆንኩላችሁ!
አፈር ቀረበታ-ታ!
አፈርሳታ-ታ!
መጨረሽታ-ታ!

Read 2579 times