Monday, 05 February 2018 00:00

የፕ/ር ሪቻርድ ፓንክረስትን ውለታ የሚዘክር ሲዲ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

  የኢትዮጵያ ወዳጅና ባለውለታ የነበሩትን የፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ታሪክ የሚዘክር በድምፅና በምስል የተቀናበረ ኦዲዮ ሲዲ፣ በተወዳጅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን የተዘጋጀ ሲሆን የፊታችን አርብ በጀርመን የባህል ማዕከል (ጎተ) እንደሚመረቅ ጋዜጠኛ እዝራ እጅጉ ገለፀ፡፡ የ68 ደቂቃ ርዝመት ያለው ይህ ሲዲ እንዲሰራ ምክንያት የሆነው ፕሮፌሰሩ የኢትዮጵያ ወዳጅና ባለውለታ ቢሆኑም ስለ እርሳቸው በአማርኛ የተፃፈ መፅሀፍም ሆነ በሌላ መንገድ የተደራጀ መረጃ ባለመኖሩ፣ ይህንን ክፍተት ለመሙላት እንደሆነ ጋዜጠኛው ገልጿል፡፡
በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር  ዶ/ር ሂሩት ወ/ማርያምን ጨምሮ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ምሁራን፣ የፕሮፌሰሩ ወዳጅና አድናቂዎች፣ ባለቤታቸው ሪታ ፓንክረስትና ሌሎች ቤተሰቦቻቸው እንደሚገኙም ታውቋል፡፡ ሲዲው በ100 ብር ለሽያጭ ይቀርባል ተብሏል፡፡

Read 2456 times