Sunday, 11 February 2018 00:00

“ፍኖተ - ሕይወት” ግለ ታሪክ መፅሐፍ ተመረቀ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

     የእውቁ ሥራ ፈጣሪና የጊዮን ኢንደስትሪያል ግሩፕ መስራቹን የአቶ ወልደሔር ይዘንጋውን የህይወት ታሪክ የሚዳስሰው “ፍኖተ - ህይወት” (የህይወት መንገድ) የተሰኘው መፅሐፍ ትላንት ምሽት ከ12፡30 ጀምሮ በሂልተን ሆቴል ተመረቀ፡፡
መፅሐፉ ባለሀብትና ስራ ፈጣሪው ከትውልድ መንደራቸው ጎጃም መርጦ ለማሪያም ፈረስማዳ ከተባለችው የገጠር መንደር ተነስተው በንግዱ ዓለም ያለፉትን ትግልና ውጣ ውረድ እንዲሁም አሁን ያሉበትን ደረጃ የሚያስቃኝ ነው፡፡ በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል፡፡ ዶ/ር ስርግው ገላውና ረዳት ፕሮፌሰርና የታሪክ ምሁሩ አበባው አያሌው በመፅሀፉ ላይ ሙያዊ አስተያየት የሰጡ ሲሆን ሌሎች ኪነ ጥበባዊ ስራዎችም ቀርበዋል፡፡
በ329 ገፆች ተቀንብቦ በ79 ብር ከ23 ሳንቲም ለገበያ የቀረበው መፅሐፉ ገቢው ሙሉ ለሙሉ ባለሀብቱ ጎጃም መርጦ ለማሪያም ላይ ቅኔ እንዳይጠፋ ለሚማሩና ለሚያስተምሩ እንዲሁም ላቋቋሙት ፋውንዴሽን ይውላል ተብሏል፡፡

Read 911 times