Sunday, 11 February 2018 00:00

“ድሮና ዘንድሮ” የፍቅረኞች የመዝናኛ ፕሮግራም ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

  በየዓመቱ የሚከበረውን የፍቅረኞች ቀን (ቫላንታይንስ ዴይ) ምክንያት በማድረግ፣ “ድሮና ዘንድሮ” የተሰኘ የመዝናኛ ልዩ የእራት ፕሮግራም በኔክሰስ ሆቴል የፊታችን ረቡዕ ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ ይካሄዳል፡፡ አብርሃም ግዛው ኢንተርቴይንመንትና የህትመት ስራዎች ድርጅት ባዘጋጀው በዚህ የፍቅረኞች የመዝናኛ ፕሮግራም ላይ በትላልቅና ታዋቂች፣ አርቲስቶች የሚቀርብ የፍቅር ገጠመኝ፣ ሳልሳና ትዊስት ዳንሶች፣ ግጥም፣ መነባንብ፣ ወግና ስታንዳፕ ኮሜዲ እንደሚቀርብ ታውቋል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ ለሚታደሙ ጥንዶች ምግብና መጠጥን ጨምሮ 1300 ብር የሚያስከፍል ሲሆን ትኬቱ ቶቶት የባህል ምግብ አዳራሽ አጠገብ በሚገኘው ኔክሰስ ሆቴል እንደሚገኝም ታውቋል፡፡  

Read 1929 times