የአድዋ በዓል ላይ ልዩ ዝግጅቱን ያደረገው 79ኛው “ግጥም በጃዝ” የኪነ ጥበብ ምሽት፣ የፊታችን ረቡዕ ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ በራስ ሆቴል ይካሄዳል፡፡
በምሽቱ ፕሮግራም ዶ/ር ዓለማየሁ አረዳ ዲስኩር የሚያቀርቡ ሲሆን ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ ገጣሚና ጋዜጠኛ ነቢይ መኮንን፣ ዶ/ር ይርጋ ገላው፣ አርቲስት አለማየሁ ታደሰ፣ ምንተስኖት ማሞ፣ ይታገሱ ጌትነትና ሚካኤል ሚሊዮን ስራቸውን ያቀርባሉ ተብሏል፡፡ በዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ ደራሲነት የተሰናዳ አጭር ተውኔት በአርቲስት ሽመልስ አበራና እታፈራሁ መብራቱ እንደሚተወን ታውቋል፡፡
Sunday, 11 February 2018 00:00
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና