Sunday, 11 February 2018 00:00

አንበሳ ባንክ፤ የወኪል ባንክ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ከአንድ መቶ ሺህ በላይ መድረሱን አስታወቀ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

     በ1999 ዓ.ም የተመሰረተውና ቅርንጫፎቹን ወደ 180 ያሳደገው አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የወኪል ባንክ አገልግሎቱ ከአንድ መቶ ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተጠቃሚዎች በመላ አገሪቱ ማዳረስ መቻሉን አስታውቋል፡፡
ባንኩ በላከው መግለጫ፤ የአንበሳ የወኪል ባንክ አገልግሎት መስጫ ሲስተምን ከመደበኛ የባንክ አገልግሎት መስጫ ሲስተም ጋር በማስተሳሰር፣ ደንበኞች የባንኩ ወኪሎች በሌሉበትም ወይም ከስራ ሰዓት ውጭ ሂሳባቸውን ማንቀሳቀስ እንደሚችሉ ጠቁሟል፡፡
በአሁኑ ወቅት ከ1 ሺህ 600 በላይ ወኪሎችና በአንበሳ ሄሎ ካሽ ክፍያ የሚቀበሉ 300 በላይ የንግድ ተቋማት በባንኩ የሚገለገሉ ሲሆን ከነዚህም መካከል የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ሰላም ባስ፣ ኤድናሞል ሲኒማ፣ መኪና ኔት እና ሌሎችም እንደሚገኙ አስታውቋል፡፡ በአንበሳ ሄሎ ካሽ አማካኝነትም ደንበኞች በአቅራቢያቸው በሚገኝ ቅርንጫፍ፣ ገንዘብ ወጪና ገቢ ማድረግ፣ የአንበሳ ሄሎ ካሽ ሂሳብ ላለውም ሆነ ለሌለው ሰው ገንዘብ ማስተላለፍ፣ የአውሮፕላንና የባስ ትኬት መቁረጥ፣ የሲኒማ ቤት ትኬት መቁረጥ፣ የሞባይል ካርድ መሙላት፣ ገንዘብ መቀበልና ማስተላለፍ እንደሚቻል ተገልጿል፡፡

Read 3604 times