Sunday, 25 February 2018 00:00

የእነ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት አዲስ ፓርቲ፣ የመስራች ጉባኤውን ያካሂዳል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

  በቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እየተደራጀ ያለው “የኢትዮጵያውያን ሃገር አቀፍ ንቅናቄ” ፓርቲ በመጪው መጋቢት 16 ቀን 2010 ዓ.ም የመመስረቻ ጉባኤውን በአዲስ አበባ እንደሚያካሂድ ታውቋል፡፡
ስለ ፓርቲው የመመስረቻ ጉባኤ ለአዲስ አድማስ የገለፁት የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፤ ፓርቲውን ለመመስረት አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን ከምርጫ ቦርድ ማግኘታቸውን አስታውቀዋል፡፡
በሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት በእርቅ ለመፍታት የተደረገው ጥረት አለመሳካቱን ተከትሎ አዲስ ፓርቲ ለመመስረት የወሰኑት የእነ ኢንጅነር ይልቃል ቡድን፣ ከቀድሞ የፓርቲው አባላት በተጨማሪ አዳዲስ ወጣቶችና ሴቶችን በስፋት ማሳተፋቸውን ገልፀዋል፡፡
ፓርቲው በአጭር ጊዜ ውስጥ የሀገሪቱ ዋነኛ የፖለቲካ ተዋናይ እንዲሆን ጠንካራ ስራዎችን እንደሚያከናውኑ ኢ/ር ይልቃል ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡

Read 1441 times