Saturday, 24 February 2018 12:27

ጋዜጠኛ ብሩክ እንዳለ ለውጭ ህክምና 850 ሺ ብር ያስፈልገዋል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

“በአፋጣኝ ህክምና ካላገኘ ጤናው አደጋ ላይ ይወድቃል”
            
    በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) በመዝናኛ ፕሮግራሞች አዘጋጅነት ያገለገለውና ለአጭር ጊዜ በጄቲቪ ኢትዮጵያ በፕሮዳክሽን ክፍል ሃላፊነት የሰራው የ28 ዓመቱ ወጣት ጋዜጠኛ ብሩክ እንዳለ፤ በዲስክ መንሸራተት ህመም እየተሰቃየ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን በአፋጣኝ ወደ ውጭ አገር ሄዶ ህክምና ካላገኘ ጤናው አደጋ ላይ እንደሚወድቅ ተጠቁሟል፡፡ ለውጭ አገር ህክምናውም ወደ 850 ሺ ብር ገደማ ያስፈልገዋል ተብሏል፡፡
የዚህን ወጣት ጋዜጠኛ ህይወት ለማትረፍ አምስት አባላት ያሉት የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን የኮሚቴው አባላት ባለፈው ረቡዕ ከሰዓት በኋላ በኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ለህክምናው ወጪ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ለማሰባሰብ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡ የጤናው ሁኔታ አስጊ ደረጃ ላይ በመድረሱም በቶሎ ገንዘብ የሚያገኙበትን ዘዴ እያፈላለጉ መሆኑንም የኮሚቴው አባላት ገልጸዋል፡፡
ከአንድ ብር ጀምሮ ሁሉም ሰው የአቅሙን በማድረግ፣የወጣቱን ጋዜጠኛ ህይወት እንዲታደገው ጥሪ ያቀረቡት የኮሚቴው አባላት፤በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000043925684፣ በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ደግሞ በhttp://gofundme.com/brick-endale-m84፣ ድጋፋቸውን እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡ ጋዜጠኛውን በቀጥታ ለማግኘት በ0912602187 ወይም በ0910880950 በመደወል ድጋፍ ማድረግ እንደሚቻልም ተጠቁሟል፡፡

Read 1252 times