Print this page
Saturday, 24 February 2018 12:38

“አይኔን ተመልከተኝ” ኦቲዝም ተኮር መፅሐፍ ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሳይካትሪ ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር በሆኑት ዶ/ር ዮናስ ባህረጥበብ የተፃፈውና በኦቲዝምና ችግሮቹ ላይ አተኩሮ የተሰናዳው “አይኔን ተመልከተኝ”  የተሰኘው መፅሐፍ፣ ዛሬ ከቀኑ 10፡30 ጀምሮ በአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴዝ ይመረቃል፡፡
በምርቃት ስነ - ስርዓቱ ላይ የህክምና ባለሙያዎች፣ የኦቲዝም ተጠቂ ህፃናትና ቤተሰቦቻቸው፣ ጥሪ የተደረገላቸው የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና ሌሎች እንግዶች የሚገኙ ሲሆን በችግሩ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ንግግሮች፣ ውይይቶችና የኪነ - ጥበብ ስራዎች ለታዳሚው እንደሚቀርቡም የምርቃቱ አዘጋጅ ይሳቃል ኢንተርቴይንመንት በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

Read 1814 times