Saturday, 24 February 2018 12:51

የድንገተኛ ቀዶ ህክምና አገልግሎት እና ባለሞያዎች ግምገማ

Written by  አዲሱ ደረስ፤ ኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

  ውድ የኢሶግ አምድ አንባቢዎች፤ የኢትዮጲያ የጽንስና ማህጸን ሃኪሞች ማህበር 26ኛ አመት ክብረበዐል እና ጉባዔ መካሄዱን ተከትሎ በዝግጅቱ ላይ ከቀረቡ ጥናቶች መካከል አንዳንዶችን እያስነበብናችሁ እንገኛለን። ለዛሬም በማህበሩ አስተባባሪነት በአገሪቱ የህክምና ተቋማት ውስጥ በሚሰጡ የድንግተኛ የቀዶ ህክምና አገልግሎት አና ባለሞያዎች ላይ የተደረገውን ግምገማ የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት ላይ ተመስርቶ በዝግጅቱ ላይ በዶ/ር እያሱ መስፍን የቀረበውን ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡
የቀረበው የጥናቱ ውጤት የተቀናጀ የድንገተኛ ቀዶ ህክምና ትምህርት በኢትዮጲያ የፌደራል ጤና ጥበቃ አማካኝነት በድህረ ምረቃ ደረጃ እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ2009 ጀምሮ መሰጠት መጀመሩን አስታውሶ አላማውም ባለሞያዎችን አሰልጥኖ በማሰማራት የጽንስና ማህጸን ማለሞዎች በማይኖሩበት ወይም በማይዳረሱበት ሁኔታ ውስጥ ከወሊድ/ ከእርግዝና ጋር የተገናኙና አጠቃላይ የድንገተኛ ቀዶ ህክምና አገልግሎት እንዲሰጡ በማስቻል የችናቶች እና የጨቅላ ህጻናትን ሞት መቀነስ ነው፡፡
እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ2012 ጀምሮ የድንገተኛ ቀዶ ህክምና ባለሞያዎች መሰማራት መጀመራቸውን ትናቱ አስታውሶ ጥናቱ በ96 ተቋማት ውስጥ በተሰማሩ 205 የሚሆኑ ባሞያዎችን አንዳካተተ ይጠቅሳል፡፡
የጥናቱ አጠቃላይ አላማ የድንገተኛ ቀዶ ህክምና ባለሞያዎች በተሰማሩባቸው ተቋማት ውስጥ ያላቸውን ሚና ለመገምገም ሲሆን በተጨማሪም አገልግሎቱ የሚሰጥባቸው የስራ አካባቢዎች ምቹነትን፤ የተቋማቱ ለአገልግሎቱ ያላቸው ዝግጁነትን፤ አስተዳደረራዊ ችግሮችን እና እንቅፋቶችን መለየት፤ አገልግሎቱ በአንድ አመት ልዩነት ያመጣቸውን ለውጦችና በተዘዋዋሪም የአገልግሎት ሰጪዎችን ክህሎት ለመገምገም ነው፡፡
ጥናቱ በተቋማ ውስጥ ከገመገማቸው ጉዳዮች አንዱ የመረጃ አያያዝ ሁኔታን ሲሆን በግኝቱም የአገልግሎት ተጠቃሚዎችን ምርመራ በተመለከተ ከተገመገሙት 93 ተቋማት 48ቱ ወይም 51.6 በመቶ የሚሆኑት መረጃ የሚይዙ መሆናቸውን፤ የበሽተኞች ክትትልን በተመለከተ ደግሞ ከተገመገሙት 92 ተቋማት 28ቱ ወይም 30 በመቶ የሚሆኑት፤ የቀዶ ህክምራን በተመለከተ ደግሞ ከተገመገሙት 91 ተቋማት 26 ወይም 28.6 በመቶ የሚሆኑት መረጃን እንደሚይዙ ግኝቱ አመላክቷል፡፡  
ተድንገተኛ ቀዶ ህክምና ባለሞያዎች ብቻ ባሉባቸው እና የቀዶ ከህክምና ባለሞያዎች በተጨማሪ የጽንስና ማህጸን ባለሞያዎች ባባቸው ሁለት አይነት ተቋማት ውስጥ በተደረገው ግምገማ ጥናቱ አብዛኞቹ ውስብስብ የጤና እክሎች ማለትም 90.7 በመቶ የሚሆኑት ማስቀረት የሚቻሉ እክሎች መሆናቸውን በግኝቱ አመላክቷል፡፡ በተጨማሪም በተገመገሙት ተቋመት ውስጥ የታዩት ውስብስብ የጤና እክሎች ውስጥ አብዛኞቹ ማለትም 86.3 በመቶ የሚሆኑት አግባብነት ያለው ህክምና ማግኘታቸውን ያሳያል።
በወሊድ ምክኒያት የሞቱ እናቶች በተመለከተ ከ63 ተቋማት ውስጥ 170 የሚሆኑ የእናቶች ሞትን አግኝቻለው ያለ ሲሆን እነዚህም ሞቶች የተመዘገቡት 32 የሚሆኑት የድንገተኛ የቀዶ ህክምና ባለሞያዎች ብቻ ባሉበት ተቋማት ውስጥ ሲሆን 31 የሚሆኑት ደግሞ የድንገተኛ የቀዶ ህክምና ባለሞያዎች በተጨማሪም ሌሎች የጽንስና ማህጸን ባለሞዎች ባለባቸው ተቋማት ውስጥ ነው ይላል፡፡
እናቶች ከመሞታቸው በፊት አስፈላጊው ህክምና ተደርጎላቸው እንደሆነ ለማወቅ በተደረገው ግምገማ የድንገተኛ የቀዶ ህክምና ባለሞያዎች ብቻ ከሚገኙባቸው 52 ተቋማት ውስጥ 29 የሚሆኑት ወይም 55.8 በመቶ የሚሆኑት አስፈላጊውን ህክምና እንደሰጡ ያሳየ ሲሆን በተጨማሪም የድንገተኛ የቀዶ ህክምና ባለሞያዎች በተጨማሪም ሌሎች የጽንስና ማህጸን ባለሞዎች ካሉባቸው 105 ተቋማት ደግሞ 67 የሚሆኑት ወይም 63.8 በመቶው አስፈላጊውን ህክምና እንደሰጡ ጠቁሟል፡፡
ሞቶቹን ካስከተሉት ምክኒያቶች ውስጥ ዋንኛ ተደርጎ የተወሰደው ወደጤና ተቋማት ለመድረስ የሚወስደው ጊዜ መዘግየት ሲሆን ይህም ከ130 ሞቶች ውስጥ 83ቱን ማለትም 63.8 በመቶ የሚሆኑትን እናቶች ህይወት እንደቀጠፈ ማወቅ ተችሏል፡፡ ወደተቋማት ዘግይተው ለሚደርሱ እናቶች የሚሰጠው የህክምና አይነት ሁለተኛው የሞት ምክኒያት ተደርጎ የተመዘገበ ሲሆን የድንገተኛ የቀዶ ህክምና ባለሞያዎች ብቻ ከሚገኙባቸው 143 ተቋማት ውስጥ በ7ቱ ማትም 16.3 በመቶ በሚሆኑት ሁለተኛ የሞት ምክኒያት ሲሆን የድንገተኛ የቀዶ ህክምና ባለሞያዎች በተጨማሪም ሌሎች የጽንስና ማህጸን ባለሞዎች በሚገኙባቸው 87 ተቋማት ውስጥ ደግሞ በ10ሩ ማለትም 11.5 በመቶ በሚሆኑት እንደሁለተኛ የሞት ምክኒያት ተደርጎ ተወስዷል፡፡
ጥናቱ በማጠቃለያውም የድንገተኛ የቀዶ ህክምና ባለሞያዎች በተቋማት ውስጥ መሰማራት ለእናቶች እና ለጨቅላዎች እንዲሁም ለድንገተኛ የቀዶ ህክምና አገልግሎት በከፍተና ደረጃ መጨመር የነበረውን አስተዋጽኦ አሳይቷል። በዚህም ምክኒያት ድንገተኛ የቀዶ ህክምና አገልግሎት በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን ጠቁሟል፡፡
ጥናሩ ችግሮች ያላቸውንም ለይቶ ያሳየ ሲሆን ከነዚህም መካከል የተተኪ ደም እጥረት፤ ከቀዶ ህክምና ጋር የተያያዙ ቁሳቁሶች እጥረት፤ የህክምና እና የቀዶ ህክምና ክህሎት እጥረት እንዲሁም ለባሞያዎች የሚሰጠው ክፍያና ማበረታቻ አገልግሎቱ ከዚህ በላይ እንዳይዳረስ እንቅፋት የሆኑ ችግሮች ሎሆኑ እንደሚችሉ ጠቁመቋል። በስተመጨረሻም ጤና ጥበቃ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በድንገተኛ የቀዶ ህክምና ስልጠና አማካኝነት ለነዚህ ችግሮች ጊዜያዊ ምላሽ ሊሰጥ እንደሚገባ እንዲሁም ከስምሪትም በኋላ ለባለሞያዎች ተከታታይ ሙያዊ ስልጠና ሊሰጥ እንደሚገባ መክሯል፡፡

Read 1216 times