Saturday, 03 March 2018 11:04

የኢሶግ፤ አኮግ ሰርት የትብብር ፕሮግራም

Written by  አዲሱ ደረስ፤ ኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

 የኢትዮጲያ የጽነስና የማጸን ሃኪሞች ማህበር ከየአሜሪካ የጽንስና ማህጸን ኮሌጅ እና ከአለም አቀፍ የስነተዋልዶ ጤና ስልጠና ማዕከል ጋር በመተባበር የጀመሩት የትብብር ፕሮጀክት ወደሁለተኛ አመቱ ተሸጋገረ፡፡
እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2016 የተጀመረው የትብብር ፕሮጀክት ሰጀመር በሶስት የትኩረት ነጥቦች ላይ አተኩሮ የተጀመረ ሲሆን እንዚህም፡ በኢትዮጲያ የጽንስና ማህጸን ህክምና የድህረ ምረቃ ፕሮግራምን ማጎልበት፤ የተከታታይ የህክምና ባለሞያዎች ስልጠናን መደገፍ እንዲሁም የመማህበሩን የስነተዋልዶ ጤና የጥናትና ምርምር መጽሄት ማጎልበት በሚሉ ሶስት የትኩረት ነጥቦችን መሰረት አድርጎ የተጀመረ ነው፡፡
በመቀጠልም ሌሎች ስድስት የሚሆኑ የትኩረት ነጥቦችን ጨምሮ ማለትም የማበሩን የቴክሎጂ እና ኢንፎርሜሽን አቅም ማጎልበት፤ የማበሩን አባላት የስራ አመራር ብቃት ማጎልበት፤ የጽንስና ማህጸን ህክምና ትምህርትን ዕውቅና የሚሰጥና ወጥ የሆነ ፈተና የሚሰጥ ጠቋም እንዲኖር የሚደረገውን ጥረት መደገፍ፤ የጽንስና ማህጸን ህክምና ባለሞያዎች ዘንድ ያለውን የሙያ ስነምግባር እንዲሁም የፍትህ አሰጣጥ ሁኔታ ለማሻሳል የሚደረገውን ጥረት መደገፍ፤ የማህበሩን የኮሙኒኬሽን እና ፕግራ ግንኙነት አቅም ማጎልበት እንዲሁም የማበሩን ተቋማዊ አቅም መገንባት ናቸው፡፡
ማህበሩ ወደሁለተኛ አመቱ በተሸጋገረበት ወቅት የተሌዩ መልካም ውጤቶችን ማስመዝገቡን የትብብር ፕጀክቱን የተለያዩ ንዑስ ፕሮጀክቶችን የሚመሩ ባሞያዎቸች ገልጸዋል፡፡ በዚህም መሰረት የትብብር ፕጀክቱ ስያሜ በሆነው የጽንስና ማህጸን የድህረ ምረቃ ፕግራምን ማጎልበት በሚለው ንዑስ ፕሮጀክት በአገሪቱ የተለያዩ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚሰጡት የድህረ ምረቃ ፕግራሞች ወጥነት የሌላቸውና የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞችን ለመጀመር የብቃት መለኪያ ያልነበረ መሆኑን አይቶ ይህንንም ለመቅረፍ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፡፡ በዚህም መሰረት ፕሮግራሙ ሁሉም የትምህርት ተቋማት የሚጠቀሙበት ወጥ የትምህርት ካሪኩሉም በማዘጋጀትና የድህረ ፕሮግራሙን ለመጀመር ለሚፈልጉ ተቋማት ማሟላት የሚገባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች የሚያሳይ ዶክመንት አዘጋጅቶ በቅድሚያ በባህርዳር በተዘጋጀ የማስረከቢያ ፕግራም ላይ ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ያስረከበ ሲሆን በመቀጠልም በየተቋማቱ በመዘዋወር ለእያንዳንዱ ተቋም አስረክቧል፡፡ በዚህ ጊዜም ከተቋማቱ የጽንስና ማህጸን የትምህርት ክፍል ባለሞያዎች ጋር በመወያየት ይበልጥ ዶክመነቶች ግንዛቤን ለማዳበር አስችሏል፡፡
በትብብር ፕግራሙ ሁለተኛ ንዑስ ፕጀክት በሆነው የህክምና ባሞዎች ተከታታይ ስልጠናን መደገፍ በሚለው ደግሞ እንዲሁ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ነበሩ፡፡ ከነዚህም መሃል በአገሪቱ የተከታታይ ስልጠና ፍላጎትን ለማትናት የነባራዊ ሁኔታ ጥናት ተካሂዷል፡፡ የህክምና ባለሞያዎች የተከታታይ ስልጠናዎችን ካሉበት ቦታ ሆነው መከታተል እንዲችሉ የሚያስችል የቴክኖሎጂ መዋቅር ዝግጅት እቅድም ተጠናቋል፡፡ ይህ ንዑስ ፕሮጀክት በተጨማሪም በ26ኛው የማበሩ ዐመታዊ ጉባዔን ተከትሎ የተካሄዱትን ተከታታይ የባለሞያዎች ስልጠናን በማቀድ አስተባብሯል፡፡
የፕሮጀክቱ 3ኛው ንዑስ ፐሮጀክት የሆነው የማህበሩን የስነተዋልዶ ጤና የጥናትና ምርምር መጽሄት ማጎልበት ሲሆን በዚህም ረገድ አጥጋቢ ውጤቶችን ማስመዝገብ ተችሏል፡፡ በዚህም የመጽሄቱን የኢዲቶሪያል ቦርድ መልሶ በማቋቋም የተጀመረው የለውጥ ሂደት ከዚህ በፊት ሳይታተም የቀረን አንድ እትምን አካቶ የ2108 እትምን በአንድ ላይ በማሳተም በ26ኛው የማህሩ ጉባዔ ወቅት አቅርቧል፡፡ መጽሄቱ የብቻው የሆነ የድህረገጽ ያልነበረው ሲሆን በትብብር ፕሮጀክቱ ከመጡ ለውጦች አንዱ የመጽሄቱን አዲስ ድህረ ገጽ ማዘጋጀት መቻ ነው፡፡ ድህረገጹ ተሰርቶ በማህበሩ 26ኛ ጉባዔ ወቅት በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ወርቁ ተመርቆ ይፋ ሆኗል፡፡
በትብብር ፕሮጀክቱ ከተካተቱት ንዑስ ፕሮጀክቶች ሌላኛው ደግሞ የህክምና ባለሞያዎችን ስነምግባር እና የፍትህ አያያዝ ላይ ትኩረቱን ደረገው ንዑስ ፕሮጀክት ነው። በዚህም እዚህ ላይ አተኩሮ ሲሰራ የነበረው ኮሚቴ ረቂቅ የስነምግባር ሰነድ ያዘጋጀ ሲሆን ይህም በአባላት ውይይት ከተደረገበት በኋላ በመጪው የማህበሩ ጉባዔ ላይ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በተጨማሪም ማህበሩን እንደተቃም ለማጎልበት የአስተዳደር ማኗል ተዘጋጅቷል፡ የማህበሩን የኮሙኒኬሽን ስራዎች አቅጣጫ ለማሲያዝም የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ ተዘጋጅቷል፡፡
ፕሮጀክቱ የቆይታ ጊዜው ሊጠናቀቅ ተጨቸማሪ አንድ አመት የቀረው ሲሆን እስከዚውም በየዘርፉ ተዐማሪ ውጤቶችን ያስመዘግባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Read 1080 times