Sunday, 04 March 2018 00:00

3ኛው ድርና ማግ የኪነ ጥበብ ምሽት ሐሙስ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 “ድርና ማግ” የኪነ - ጥበብ ምሽት ለ3ኛ ጊዜ የፊታችን ሐሙስ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ መገናኛ በሚገኘው አፋራንሲስ ኢንተርናሽናል ሆቴል ይካሄዳል። በተለይ የአሁኑን ምሽት ለየት የሚያደርገው የሚቀርቡት ዝግጅቶች 122ኛውን የአድዋ ድል በዓል የሚዘክሩ በመሆናቸው ነው ተብሏል፡፡
በዝግጅቱም ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ፣ ገጣሚና ተዋናይ ተፈሪ አለሙ፣ ሰዓሊና ገጣሚ አገኘሁ አዳነ፣ የሙዚቃ ባለሙያና ተመራማሪ ሰርፀ ፍሬ ስብሃት፣ እንዲሁም ገጣሚዎቹ ረድኤት ተረፈ፣ ዳንኤል ስዩምና ደሳለኝ ብርሃኑ ስራዎቻቸውን ለታዳሚው እንደሚያቀርቡ ታውቋል፡፡ መሶብ ባህላዊ ባንድ በአዳዲስ ሙዚቃዎቻቸው ዝግጅቱን አድምቀው እንደሚያመሹም የፕሮግራሙ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ዓለሙ አስታውቋል፡፡

Read 3566 times