Print this page
Saturday, 03 March 2018 12:35

“የኢትዮጵስ ተረቶች ቁጥር 1” የተረት መፅሐፍ ነገ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(8 votes)

በኢቢኤስ ቴሌቪዥን የሚተላለፈው “ኢትኦጵስ” የልጆች ፕሮግራም አዘጋጆች አንድነት አማረ፣ ይትባረክ ዋለልኝ፣ እና ሳምሶን መረሳ የተሰናዱ ተረቶችን የያዘው “የኢትዮጵያ ጣፋጭ ተረቶች ቁጥር 1” መፅኀፍ ነገ ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ ቦሌ በሚገኘው “ዴይ ላይን አዲስ” የልጆች መጫዎቻ ማዕከል ይመረቃል በምስልና በሙሉ ቀለም አሸብርቆ የተሰራውና ተለቅ ያለ መጠን ያለው መፅሀፍ ሶስት ተረቶችን እንደያዘም ለማወቅ ተችሏል፡፡ በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ደራሲ እንዳለ ጌታ ከበደ፣ ዳንኤል ወርቁና ኮሜዲያን አስረስ በቀለን ጨምሮ ሌሎችም ደራሲዎች የሚታደሙ ሲሆን ከመፅሀፉ ላይ ለልጆች ተረቶች ያነባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።
በ14 ገፅ የተመጠነው መፅሀፍ በ40 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን በምርቃቱ ላይ ወላጆች ልጆቻቸውን በመያዝ ከኢትዮጵስ ጋር ጥሩ ጊዜ እንዲያሳልፉ ጥሪ ቀርቧል፡፡

Read 6894 times