Sunday, 04 March 2018 00:00

“የአፀዱ ትርምስ” የግጥም መፅሀፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(10 votes)

የበባህር ዳር ነዋሪ ወጣት ገጣሚ መብራቱ ከፍ ያለው የፃፋቸው ግጥሞች የተሰባሰቡበት “የአፀደ ትርምስ” የግጥም መድብል ሰሞኑን ለንባብ በቃ፡፡ የገጣሚው ስራዎች ሰፊ አስተውሎትና የተባ ምናብ የሚታይባቸው፣ ምርጥና ያልተለመዱ አዳዲስ ቃላትን በስፋት የሚጠቀም ሲሆን፣ ግጥሞቹ በአሰናኘታቸው እንደ አብዛኞቹ የዘመናችን ግጥሞች ፉት የምንላቸው ሳይሆኑ ሳብ አድርገን የምንጎነጫቸውና ጥምን የሚቆርጡ መሆናቸው የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ስነ ፅሁፍ እንዲሁም የስነ ልሳንና ፊሎሎጂ ባለሙያው ሊቀ ህሩያን በላይ መኮንን በመፅሀፉ የጀርባ ሽፋን ላይ ያሰፈሩት ማስታወሻ ይጠቁማል፡፡
መፅሐፉ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በጥልቀት የተቀመሩ በርካታ ግጥሞችን የያዘ ሲሆን በ136 ገፆች ተቀንብቦ፤ በ49 ብር ከ90 ሳንቲም ለገበያ ቀርቧል፡፡
ገጣሚው ከዚህ ቀደም “አስፈሪ ዝምታ” የተሰኘ የግጥም መፅሀፍ ለንባብ ማብቃቱ የሚታወስ ሲሆን “የአፀዱ ትርምስ” የተሰኘው አዲሱ መፅሐፍ፤ በቅርቡ በባህርዳር ከተማ ለምርቃት እንደሚበቃ ገጣሚ መብራቱ ለአዲስ አድማስ ገልጿል፡፡

Read 8768 times