Saturday, 28 April 2012 13:22

የፒያኖና ጊታር ድግስ ዛሬ ይቀርባል “አሳትፋኝ” ዛሬ ይጀመራል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

ሕይወት የሙዚቃ ትምህርት ቤት ያዘጋጀውና ከ4 እስከ 16 ዓመት እድሜ ያሉ ታዳጊ ወጣቶች የሚሳተፉበት የፒያኖና የጊታር ሙዚቃ ድግስ ዛሬ ይቀርባል፡፡ በጣሊያን የባህል ተቋም የሚቀርበውን ድግስ ያዘጋጁት የሙዚቃ ባለሙያና የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህርት ወይዘሮ ሕይወት ማሞ ናቸው፡፡ ከቀኑ 9 ሰዓት ተጀምሮ እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት የሚዘልቀው ዝግጅት፤ በሦስት ምድብ ከአራት ዓመት እስከ ስምንት ዓመት፣ ከዘጠኝ ዓመት እስከ 11 ዓመት እና ከ12 ዓመት እስከ 16 ዓመት ያሉ ሕፃናት ሥራዎቻቸውን የሚያቀርቡበት ነው፡፡ ወይዘሮ ሕይወት ካሁን ቀደም የሕፃናት ዲቪዲ መዝሙር እና የሕፃናት መፃሕፍት በማዘጋጀት ይታወቃሉ፡፡

የዛሬው የሙዚቃ ድግስ እንግዳ፣ የሙዚቃ ባለሙያ ሠርፀ ፍሬስብሃት መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ “አሳትፋኝ” የወጣቶች ፊልም አውደርዕይ ዛሬ ይጀመራል፡፡ ከጧቱ 2፡30 ላይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር የሚጀመረውን ዝግጅት የሚያቀርቡት “ሴቭ ዘ ቺልድረን ዴንማርክ” እና “ዊዝ ኪድስ ዎርክሾፕ” ናቸው፡፡ በአውደርእዩ የ36 ወጣት ፊልም ሠሪዎች ሥራዎች ይቀርባሉ፡፡

 

 

Read 1219 times Last modified on Saturday, 28 April 2012 13:26