Print this page
Tuesday, 20 March 2018 11:17

ኢቢኤስ፣ ቃና፣ ናሁ እና ኤልቲቪ ፍቃድ ሊሰጣቸው ነው

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

 *የግል ኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች ጨረታ ወጥቷል
               
    ኢቢኤስ፣ ቃና፣ ናሁ እና ኤልቲቪ የሚጠበቅባቸውን ህጋዊ መስፈርት በማሟላታቸው ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ፍቃድ ሊሰጣቸው መሆኑ ታውቋል፡፡
ጣቢያዎቹ ቀደም ሲል ፍቃድ ለማግኘት የተቸገሩት በዜግነት ኢትዮጵያዊ ባልሆኑ ግለሰቦች ባለቤትነት የተያዙ ስለነበሩ ነው ተብሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት ባለቤትነታቸው በኢትዮጵያውያን እንዲሆን ከጣቢያዎቹ ጋር ውይይት እየተደረገ መሆኑን የገለፀው ባለስልጣኑ፤ የንብረቶቹ ባለቤት ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው አካል እንዲሆን ተደርጎ ፍቃዱ ይሰጣቸዋል ተብሏል፡፡
ቀደም ሲል ጣቢያዎቹ ህጋዊ ፍቃድ ሳይኖራቸው እየሰሩ መሆኑ በብሮድካስት ባለስልጣን መገለፁ የሚታወስ ሲሆን ከዚያ በኋላ በተደረጉ ውይይቶች መስፈርቶቹን ለማሟላት በመስማማታቸው  ህጋዊ እውቅና እንደሚያገኙ ተነግሯል፡፡
በሌላ በኩል ብሮድካስት ባለስልጣን የግል የኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች መክፈት ለሚፈልጉ  ጨረታ ማውጣቱም ታውቋል፡፡

Read 1645 times