Tuesday, 20 March 2018 11:19

“ከዕለታት አንድ ቀን” የግጥም መድበል ለንባብ ቀረበ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

“ኧረ በሬን ዝጉት
 ይጨልም ጓዳዬ
 ብቸኝነቴ ነው
 የዛሬ እንግዳዬ
 እስቲ ላነጋግረው
 በፅልመት ተውጬ
 የውስጤን ቃጠሎ እስካይ ገላልጬ፡፡”
ከላይ የተነበበው ግጥም ሰሞኑን ለገበያ ከቀረበው “ከዕለታት አንድ ቀን” የተሰኘ የግጥም መድበል ውስጥ “ገላልጩ” በሚል ርዕስ የሰፈረ ነው፡፡ የግጥሞቹ ፀሐፊ ሳምሶን ከፍያለው ሲሆን መፅሐፉ በ91 ገፆች 60 ግጥሞችን አካቶ ይዟል፡፡
ገጣሚው በመግቢያው ላይ ባሰፈረው ሃተታ፤ “የመፅሐፌን ገፅ የተጋሩ 60 ግጥሞች፤ የ60 ነፍሳት እስትንፋስ እስኪመስሉ ድረስ ውስጤ እያቃሰቱ ከርመዋል፡፡ ሥነ ግጥም በቃላት ከሽኖ ህይወት ባይዘራባቸው ኖሮ የትኛው ጥበብ ከጭንቀቴ እንደሚገላግለኝ አላውቅም ነበር” ብሏል፡፡
ፋር ኢስት ትሬዲንግ ያሳተመው የግጥም መድበሉ፤ በ50 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 1294 times