Print this page
Saturday, 14 April 2018 13:44

የዋልድባ መነኮሳት ትናንት ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተለቀዋል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

 የዋልድባ ገዳም መነኮሳትን ጨምሮ ክሳቸው የተቋረጠላቸው 114 የሽብር ተጠርጣሪዎች ሰሞኑን ከእስር መፈታታቸው ታውቋል፡፡  በእነ ተሻገር ወ/ሚካኤል በሚል የክስ መዝገብ ስር፣ የወልቃይት የስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክትን ለማስተጓጎል ተንቀሳቅሰዋል በሚል በሽብር የተከሰሱት ሁለቱ መነኮሳት አባ ወ/ሥላሴ እና አባ ገ/ኢየሱስ ናቸው፡፡
ከሁለቱ መነኮሳት ጋር አብረው ከተከሰሱት 35 ግለሰቦች ውስጥ 33ቱ አስቀድሞ ክሳቸው ተቋርጦ የተፈቱ ሲሆን ሁለቱ መነኮሳትን ጨምሮ በተለያዩ የሽብር ጉዳዮች የተከሰሱ ግለሰቦች ትናንት ቀትር ላይ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ወጥተዋል፡፡  መነኮሣቱ በታሰሩበት ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ኢ-ሰብአዊ አያያዝ እንደሚያጋጥማቸው በተለያዩ ጊዜያት ሲገልጹ የቆዩ ሲሆን የምንኩስና ልብሳቸውን በሃይል እንዲያወልቁ መጠየቃቸውንም ለፍ/ቤት አመልክተው ነበር፡፡
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የመነኮሳቱን ጉዳይ የሚከታተሉ ምዕመናን፣በፍ/ቤት እየተገኙ ድጋፋቸውን ሲገልፁላቸው የቆዩ  ሲሆን ከእስር እንዲፈቱም ከፍተኛ ግፊትና ዘመቻ ሲደረግላቸው እንደነበር ይታወቃል፡፡ በሌላ በኩል፤የመነኮሳቱ ጉዳይ በቀጥታ የሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደርና ቅዱስ ሲኖዶስ  ድምጻቸውን አጥፍተው፣ በዝምታ መመልከታቸው፣ ለብዙዎች እንግዳ ሆኖ ቆይቷል፡፡   
በዋልድባ ገዳም አካባቢ ለማቋቋም የታቀደው የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክት፤በሃገር ውስጥ እና በውጪ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን፣ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞት እንደነበር ይታወሳል፡፡

Read 3412 times