Saturday, 14 April 2018 14:57

በ“ዋናዎቻችንን እናስብ” አለቃ ገ/ሃና ሰኞ ይዘከራሉ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

ምስክር ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን “ዋናዎቻችንን እናስብ” በተሰነው መርሃ ግብሩ የዜማ የቅኔ፣ የፍልስፍናና የወግ አዋቂ የነበሩትን አለቃ ገ/ሃናን የፊታችን ሰኞ ከ11 ሰዓት ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር ይዘክራል፡፡
በዕለቱም መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል ከዜማ ስልታቸው አንፃር፣ መጋቢ ሀዲስ እሸቱ ዓለማየሁ ከቅኔ አንፃር፣ የሚዳስሷቸው ሲሆን ቀልዳቸውን ከፎክሎር አንፃር መምህር የሻው ተሰማ፣ ከምሁራዊ ስብዕናቸው አንፃር ደግሞ ሙሃዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት ዳሰሳ እንደሚያቀርቡ የምስክር ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን ባለቤትና ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ምስክር ጌታነው ገልጿል፡፡ አርቲስት ፈቃዱ ከበደ፣ ሽመልስ አበራ፣ ካሌብ ዋለልኝ - ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ወጎች ያቀርባሉ ተብሏል፡፡

Read 2445 times