Saturday, 21 April 2018 11:47

“መንግሥትና የግለሰብ ነፃነት” መፅሃፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

  በደራሲ መካሻ አበራ የተፃፈው “መንግሥትና የግለሰብ ነፃነት” መፅሀፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡ መፅሐፉ በዋናነት የብአዴን ጽ/ቤት ኃላፊ በሆኑት አቶ አለምነው መኮንን የተፃፈው “ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና የኢትዮጵያ ህዳሴ” ለተሰኘው መጽሀፍ ምላሽ የሚሰጥ ነው ተብሏል፡፡ በአምስት ዋና ዋና ምዕራፎች የተከፋፈለው መፅሃፉ በሪበራል ዴሞክራሲና ገበያ አክራሪነት፣ በምዕራባዊያን የገበያ አክራሪነትና ሊበራል ዴሞክራሲ የቀረበውን ትችት በተመለከተ አጠቃላይ እይታና በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያጠነጥን ነው፡፡ በ240 ገፅ የተመጠነው መፅሀፉ በ65 ብር እየተሸጠ ነው፡፡

Read 3669 times