Saturday, 28 April 2018 10:05

ያልተፈለገ እ ርግዝና መ ከላከያ… ፍ ላጎትና… አ ፈጻጸም…

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(2 votes)

በሁለት አመት ልዩነት አራርቆ መውለድ ወደ 10% የሚሆነውን የጨቅላ ሕጻናት ሞት እንዲሁም ወደ 21% የሚሆነውን እድሜያቸው ከ1-4 የሚደርሱ ሕጻናትን ሞት በአለም አቀፍ ደረጃ እንደሚቀንስ በጥናት ተረጋግጦአል፡፡
አብዛኛዎቹ ሰዎች እድሜያአው 25/አመት ከመድረሱ በፊት የወሲብ ግንኙነትን ይፈጽማሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ከግማሽ በላይ የሚሆነው የአለም ህዝብ እድሜው ከ25/ አመት በታች ማለትም ወደ 1.8/ቢሊዮን የሚሆኑት በ10/ እና 24/ አመት እድሜ መካከል ናቸው፡፡ ከእነዚህም አብላጫዎቹ (85%) የሚሆኑት ኑሮአቸው በመልማት ላይ ባሉ ሀገራት ነው፡፡ Journal of adolescent health እንደሚጠቅሰው በአለም አቀፍ ደረጃ 50/% ያህሉ ወጣት ሴቶች በእድሜያቸው ከ15-19/ያሉት ወሲባዊ ግንኙነትን በመፈጸም ላይ ቢሆኑም ያልተፈለገ እርግዝናን ለመከላከል አገልግሎቱን ለማግኘት ግን የተለያዩ ችግሮች አሉ፡፡
ምንጭ፡- Journal of adolescent health
በዚህ እትም የምናስነብባችሁ የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር በሚያወጣው ጆርናል የሰፈረውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዶ/ር ኃይለጊዮርጊስ አውላቸውና ሌሎች ባለሙ ያዎች በጥናት እውን ያደረጉትን በተለይም ከወሊድ በሁዋላ የቤተሰብ እቅድ ዘዴ ፍላጎትና አጠቃቀምን የሚመለከት ነው፡፡ ጥናቱ የተደረገው በአዲስ አበባ ነው፡፡
የቤተሰብ እቅድ ዘዴ የቤተሰብን ሕይወት በተሳካ መልኩ ለመምራት ከሚያስችሉ ዘዴዎች አንዱና ዋናኛው ነው፡፡ በዚህ ዘዴም የስነተዋልዶ ጤናን ማሻሻል እና እንዲሁም የእናቶችንና የህጻናትን ጤንነት መጠ በቅ ያስችላል፡፡ ያልተፈለገ እርግዝናን መከላከል ለማንኛቸውም በእድ ሜያቸው ለወሲብ ለደረሱ ሰዎች የሚያስፈልግ መሆኑ እንዳለ ሆኖ  የቤተሰብ እቅድ ዘዴን ለመተግበር በተለ ይም አራ ርቆ ለመውለድ እንዲያስችል ያልተፈለገ እርግዝናን ለመከላከል የቤተሰብ እቅድ ዘዴ አገልግሎ ቱን ማግኘት ይገባል፡፡
ሴቶች ከወለዱ በሁዋላ የቤተሰብ እቅድ ዘዴን ተግባራዊ ማድረግ እንዲያስችላቸው ያልተፈለገ እርግዝናን ለመከላከል አገልግሎቱን ካላገኙ ሁኔታውን አስቸጋሪ ያደርገዋል። ከወሊድ በሁዋላ ከ7-9/ወር ድረስ ባለው ጊዜ ሴቶች ለእርግዝና ሊጋለጡ የሚችሉበት ወቅት መሆኑ እሙን ነው። ነገር ግን በጥናቱ እንደታየው ብዙ ሴቶች ከወለዱ ከሁለት አመት በፊት በድጋሚ እር ጉዝ መሆን አይፈልጉም፡፡ በአንጻሩ ግን ያልተፈለገ እርግዝና መከላከያውን አይወስዱም፡፡ እንደ ዚህ ያሉ ሴቶች የወር አበባቸው ተመልሶ በትክክል ቢመጣም እንኩዋን ከወሲብ መታቀብን ተግባራዊ ስለማያደርጉ ተመልሰው ማርገዛቸው አይቀርም፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ በ2010/ ወደ 287.000/የሚሆን የእናቶች ሞት ተመዝግቦአል፡፡ ከዚህ ውስጥ ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት የሞቱት እናቶች ወደ 56% ሲሆኑ ምክንያታ ቸውም ከእርግዝናና ወሊድ ጋር የተያያዘ ነው። በኢትዮጵያም በ2016/እንደውጭው አቆጣጠር ተደርጎ በነበረው የ Demographic and health survey (EDHS) መረጃ እንደተመዘገበውም ከአርግዝና ጋር በተያያዘ የደረሰው ሞት 412/ይደርሳል፡፡ ከ2010/ጀምሮ 95% የሚሆኑ መካከ ለኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት ሴቶች ከወለዱ በሁዋላ ባለው ቀጣይ ሁለት አመት ልጅ እንዳይ ወለድ ለማድረግ ቢፈልጉም ወደ 70% የሚሆኑ ሴቶች መከላከያውን አልተጠቀሙም፡፡
ልጅ በተወለደ በአንድ አመት ውስጥ እርግዝና ከተከሰተ ለእናትየውም ሆነ ለተወለደው ልጅ ጤንነት አስከፊ ሁኔታን እንደሚያስከትል ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ስለዚህ ቢያንስ ቢያንስ በሁለት አመት ልዩነት አራርቆ መውለድ ወደ 10% የሚሆነውን የጨቅላ ሕጻናት ሞት እንዲሁም ወደ 21% የሚሆነውን እድሜያቸው ከ1-4 የሚደርሱ ሕጻናትን ሞት በአለም አቀፍ ደረጃ እንደሚቀንስ በጥናት ተረጋግጦአል፡፡
እስከአሁን ባለው ተሞክሮ ከወሊድ በሁዋላ ስለሚኖረው ያልተፈለገ እርግዝናና መከላከያው በፖሊሲ አውጪዎች የጤና አገልግሎት ሰጪዎች እና በራሳቸው በሴቶቹም በኩል ቢሆን በትክክል ግንዛቤው አለ ለማለት አይቻልም እንደጥናት አቅራቢዎቹ፡፡ ከወሊድ በሁዋላ ብዙውን ጊዜ ሴቶች የወር አበባቸው ሳይታይ ላልተወሰነ ጊዜ ሊቆይ እንደሚችልና አንዳንድ ጊዜም የወር አበባቸውን ሳያዩ ወይንም ጡት በማጥባት ላይ እያሉ ጭምር በዚያው እርግዝና  ሊከሰት እንደሚችል እውነታዎች ይመሰክራሉ። ከወሊድ በሁዋላ የሚያስፈልገው የእርግዝና መከላከያ በሐኪሞች ወይንም በሚገለገሉባቸው ክሊኒኮች አሰራር መሰረት ከወሊድ በሁዋላ ባሉ የ12/ ወራት ጊዜ እና የጡት ማጥባትንም ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ መሆን አለበት፡፡
በጥናቱ ከተካተቱት 833/ የሚሆኑ እናቶች ውስጥ በወለዱ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች 98.6% የሚሆኑት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ከአጠቃላይ የጥናቱ ተሳታፊዎች 192/ማለትም 23.0% የሚሆኑት ባለፈ ታሪካቸው አራርቆ ለመውለድ ቢፈልጉም ያልተፈለገ እርግዝናን መከላከል ባለመቻላቸው ጽንስን የማቋረጥ ችግር እንደደረሰባቸው ገልጸዋል፡፡ በጥያ ቄው ከተሳተፉት ውስጥ 28ቱ/ወይንም 3.4% የሚሆኑት የሞተ ልጅ ለመውለድ መገደዳቸውን ተናግረዋል፡፡ 484/ ከሚሆኑት ከአንድ በላይ እርግዝና ከነበራቸው ወስጥ 136/ወይንም 28.1% የሚሆኑት የመጀመሪያ ልጃቸውን በወለዱ በሁለት አመት ጊዜ ውስጥ በድጋሚ ወልደዋል፡፡ በጥናቱ ጥያቄ ከተጋበዙት ውስጥ 104/ወይንም 12.5% የሚሆኑት በጊዜው የነበራቸው እርግ ዝና ያልተፈለገ ወይንም ያልታቀደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በእርግጥ ወደ 64%የሚሆኑት ምንም አይነት ያልተፈለገ እርግዝና መከላከያ እንደማይጠቀሙ ጠቁመዋል፡፡
የተዋልዶ ሁኔታን በሚመለከት በጥናቱ ከተካተቱት ውስጥ ወደ 375/ 45.0% የሚሆኑት ሴቶች ልጆቻቸውን ከሁለት አመት በላይ አራርቀው መውለድ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡ በተለይም ከወሊድ በሁዋላ የህክምና ክትትል የሚያደርጉ እናቶች ባለሙያዎቹ በሚሰጡት ምክር መሰረት አራርቀው መውለድ የሚያስችላቸውን ያልተፈለገ እርግዝና መከላከያ እንደሚወስዱ ተረጋግጦ አል፡፡ ከዚህም በመነሳት ጥናቱ የደረሰበት ነገር ሴቶች ከሕክምናው አገልግሎና ምክር የማይርቁ ከሆነ በትክክለኛው መንገድ ዘመናዊ የሆነውን የቤተሰብ እቅድ ዘዴ የሚጠቀሙ መሆኑን ነው፡፡ ይሁን እንጂ ከትዳር አጋራቸው ጋር ስለቤተሰብ እቅድ ዘዴ ምክክር የማያደርጉ ከሆነ በትክክ ለኛው መንገድ አራርቀው ለመውለድ ወይንም ምን ያህል ልጅ መውለድ በቂ ነው የሚለውን ለመወሰንና ኑሮአቸውን በትክክል ለመምራት አይችሉም፡፡ ይህም በተደጋጋሚ ማርገዝ ምን ያህል ለጤና አስከፊ እንደሚሆንና ለሚወለደውም ልጅ በትክክል ጤንነቱን ለመጠበቅ አስቸጋሪ እንደሚሆን ካለመረዳት የሚያስከትለው ችግር መሆኑን ጥናቱ ያሳያል፡፡ ይህ ጥናት በተጨ ማሪም እንደሚያስገነዝበው ጥሩ አድርገው ማሳደግ የማይችሉትን ልጅ መውለድ ምን ያህል በኑሮ ላይ ጫና እንደሚያሳድር ከግንዛቤ አለማስገባትም ከቤተሰብ አልፎ በሀገር ደረጃ ውጤቱ አስከፊ ይሆናል፡፡ አንዳንድ ጊዜም ባሎች የሚስቶቻቸውን ሀሳብ የማይቀበሉ እና ድጋፍ የማይ ሰጡም ከሆነ ምናልባትም በሕክምና ተቋሙና በባለሙያዎቹ የሚሰጠው ምክር ተግባር ላይ ስለማይውል የቤተሰብ እቅድ ዘዴን በትክክል ተግባራዊ ማድረግ አይቻልም፡፡ ከዚህም በተጨ ማሪ ወንዶቹ በስራ እና በተለያዩ ምክንያቶች ሰፋ ላለ ጊዜ በቤታቸው የማይገኙ ከሆነ ወይንም የወሲብ ግንኙነቱ በተራራቀ ጊዜ የሚፈጸም ከሆነ ሴቶች የቤተሰብ እቅድ ዘዴን መጠቀም አስፈላጊ ነው ብለው እንዳያምኑ ሊያደርጋቸው ወይም ሊያዘናጋቸው እንደሚችልም በጥናቱ ተረጋግጦአል። ነገር ግን ባልየው በአመት ይሁን በስድስት ወር በቤቱ ከተገኘ ወይንም በፈለገ ጊዜ የወሲብ ግንኙነቱን ካደረገ ሚስትየው ያልተፈለገ ወይንም ባልታቀደ ጊዜ የማርገዝ እድል እንደሚኖራት መገመት ያስፈልጋል፡፡
ጥናት አድራጊዎቹ እንደገለጹት ጥናቱ በተደረገበት ወቅት ከወሊድ በሁዋላ አራርቆ ለመውለድ እንዲያስችል ወይንም ምን ያህል ልጅ መውለድ ያስፈልጋል የሚለውን ለመወሰን እንዲያስችል የእርግዝና መከላከያን በመውሰድ ረገድ በጎም ይሁን ጎጂ የሆኑ የተለያዩ ውጤቶች ተመዝ ግበዋል፡፡ እናቶች ልጅ ከወለዱ በሁዋላ የቤተሰብ እቅድ ዘዴን ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ከሚያዘናጉዋቸው ምክንያቶች …
(የወር አበባው ቶሎ ተመልሶ አለመታየቱ፤ የወሲብ ግንኙነት መፈጸሙ በተራራቀ ጊዜ መሆን አለመሆኑ፤ በሕክምና ባለሙያዎቹ የሚሰጠውን የምክር አገልግሎት በትክክል ባልና ሚስቶቹ ተመካክረው መፈጸም አለመቻላቸው፤ እናቶች ከወሊድ በሁዋላ ለምክር አገልግሎት ወደሕክምና ባለሙያ አለመቅረባቸው) የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡
ባጠቃላይም እርጉዝ የሆኑ እናቶች በቤተሰብ እቅድ ዘዴ ላይ ተገቢውን የምክር አገልግሎት ከሕ ክምና ባለሙያዎች ማግኘት እና የእውቀት ደረጃቸውን ከፍ ማድረግ እንዲሁም ለድርጊቱ ንቃት የተሞላበት ፈቃደኝነት እንዲያሳዩ ማስቻል አራርቆ ለመውለድና የቤተሰብ መጠንንም ለመወሰን ስለሚያስችል ያልተፈለገ እርግዝናን ለመከላከል እና በጥሩ አቋም ላይ የተመሰረተ ቤተሰብን ለማፍራት ያስችላል፡፡

Read 2700 times