Saturday, 12 May 2018 11:36

“ሰማያዊ” ፓርቲ፤ በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጉዳይ ይወያያል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(5 votes)

    በሽብር ወንጀል የዕድሜ ልክ ፍርደኛ ሆነው፣ በእስር ላይ የሚገኙት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በተመለከተ በዛሬው ዕለት ውይይት እንደሚያደርግ የገለፀው “ሰማያዊ” ፓርቲ፤ ነገ ደግሞ “የግጭት አፈታት ገንቢ አስተዋፅኦዎች” በሚል ርዕስ በሚቀርብ ጥናት ላይ ውይይት እንደሚያካሄድ አስታውቋል፡፡
በእስር ላይ የሚገኙት የ“ግንቦት 7” አመራር አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲፈቱ ሰሞኑን  በማህበራዊ ሚዲያዎች ሰፊ ዘመቻ ሲካሄድ የሰነበተ ሲሆን “ሰማያዊ” ፓርቲ በበኩሉ፤ መምህርት መስከረም አበራ በአቶ አንዳርጋቸው የህይወት ተሞክሮ ላይ በምታቀርበው ጥናታዊ ፅሑፍ መነሻነት ውይይት እንደሚያካሂድ ሊቀ መንበሩ አቶ የሺዋስ አሰፋ ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም በአሜሪካ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በአለማቀፍ የግጭት አፈታት መምህርነታቸው የሚታወቁት ፕ/ር ብርሃኑ መንግስቱ፤ “የግጭቱ አፈታት ገንቢ አስተዋፅኦዎች” በሚል ርዕስ በሚያቀርቡት ጥናት ላይ ውይይት ይደረጋል ተብሏል፡፡

Read 6983 times