Saturday, 26 May 2018 13:10

“ዓለም በጌታቸው ዓይን” የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽን ተከፈተ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 የዶ/ር ጌታቸው ተድላ የፎቶግራፍ ስብስቦች ለዕይታ የቀረቡበት “ዓለም በጌታቸው አይን” የተሰኘ የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ ትላንት ምሽት በብሔራዊ ቴአትር አርት ጋለሪ መከፈቱን የአውደ ርዕዩ አዘጋጅ ኢጋ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን አስታወቀ፡፡
ፎቶግራፎቹ ዶ/ር ጌታቸው ላለፉት 30 ዓመታት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ በተለያዩ ኃላፊነቶች በሰሩባቸው ጊዜያት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ሲዘዋወሩ በካሜራቸው ያስቀሯቸው የተለያዩ አገራትን ባህል፣ ታሪክ፣ መልክአ ምድርና ተያያዥ ጉዳዮች የሚያሳዩ ሲሆን አውደ ርዕዩ እስከ መጪው ቅዳሜ ድረስ ለዕይታ ክፍት ሆኖ ይቆያል ተብሏል፡፡
 ከአውደ ርዕዩ ጎን ለጎንም በፎቶግራፍና ታሪኮቻቸው ዙሪያ ለሦስት ቀናት ውይይት እንደሚካሄድ ተጠቁሟል፡፡ ዶ/ር ጌታቸው ተድላ ከዚህ ቀደም “ተድላ አበበ የዘመናዊ እርሻ ፋና ወጊ”፣ “እንደወጡ የቀሩ ኢትዮጵያዊ”፣ “የህይወት ጉዞዬና ትዝታዎቼ ቁጥር 1 እና ቁጥር 2” እንዲሁም “የአክሊሉ ማስታወሻ” የተሰኙ መፅሐፍትን ለንባብ ማብቃታቸው ይታወሳል፡፡

Read 1322 times