Sunday, 03 June 2018 00:00

“በትግራይ የፖለቲካ እስረኞች አልተፈቱም” - አረና

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

ከ50 በላይ አመራሮቹና አባላቱ በትግራይ ክልል በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች ታስረው እንደሚገኙ የገለፀው አረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ሉአላዊነት (አረና) ፓርቲ፤ የክልሉ መንግስት እስካሁን ዋነኛ የፖለቲካ ሰዎችን ከእስር አለመልቀቁን አስታወቀ፡፡
በቅርቡ ከ2 ሺህ በላይ እስረኞች በክልሉ መለቀቃቸውን ያስታወሡት የፓርቲው ም/ሊቀመንበር አቶ ጎይቶም ፀጋዬ፤ ከተለቀቁት መካከል አንድም ፖለቲከኛ አለመኖሩን ለአዲስ አድማስ አስታውቀዋል፡፡
ከ50 በላይ የሚሆኑ በፓርቲው ውስጥ ሠፊ ተሣትፎ የሚያደርጉ አባላትና አመራሮች በተለያየ ሰበብ በእስር ላይ እንደሚገኙ የገለፁት አቶ ጎይቶም፤ ፓርቲያቸው ታሣሪዎች እንዲፈቱ በተደጋጋሚ ቢጠይቅም ቀና ምላሽ አለማግኘቱን ጠቁመዋል፡፡
ከፓርቲው አባላት በተጨማሪም መሠረቱን ኤርትራ አድርጎ፣ የኢትዮጵያን መንግስት በመቃወም ከሚንቀሳቀሰው የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ ጋር ግንኙነት አላችሁ ተብለው የታሠሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦች ከእስር አለመፈታታቸውን አቶ ጎይቶም አስታውቀዋል፡፡

Read 2291 times