Sunday, 03 June 2018 00:00

መንግስት የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይልን እንዲበትን ተጠየቀ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(4 votes)

በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች ውስጥ የሠብአዊ መብት ጥሰቶችን እየፈፀመ ነው ያለውን የሶማሌ ልዩ የፖሊስ ኃይል፣ መንግስት በአስቸኳይ እንዲበትን የሠብአዊ መብት ተሟጋች ተቋም አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ፡፡
አምነስቲ ትናንትና ባወጣው መግለጫው፤ የሶማሌ ልዩ የፖሊስ ኃይል፣ ተደጋጋሚ የሠብአዊ መብት ጥሠትና ግድያዎችን እየፈፀመ መሆኑን ጠቅሶ፤ ከሠሞኑም በክልሉ 48 ቤቶችን በማቃጠል፣ ነዋሪዎች ቀዬአቸውን ጥለው እንዲሠደዱ አድርጓል ብሏል፡፡
መንግስት ይህን ልዩ የፖሊስ ኃይል፣ በአስቸኳይ በመበተን፣ ለአለማቀፍ የሰብአዊ መብቶች አጠባበቅ ተገዥ የሆነ መደበኛ የፖሊስ ሃይል እንዲደራጅ ጠይቋል፡፡
“ከዚህ በኋላ የሶማሌ ልዩ ሃይል አባላት እንዳሻቸው በህዝብ ላይ ግፍ እንዲፈፅሙ መፈቀድ የለበትም” ያለው ተቋሙ፤ “መንግስት ይሄ ጥቃት በአስቸኳይ እንዲያበቃ ማድረግ አለበት” ብሏል፡፡
በአከባቢው ላለው ግጭት ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠትም ልዩ ሃይሉን በማፍረስ፣ የክልሎችን ድንበር በተገቢው ሁኔታ ማካለል ያስፈልጋል ብሏል- አምነስቲ፡፡

Read 6861 times