ሰምና ወርቅ ሚዲያ ኢንተርቴይመንት፤ ስድስተኛውን የኪነጥበብ ምሽት የፊታችን ሐሙስ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ መገናኛ ፓናሮማ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው ቫምዳስ መዝናኛ ማዕከል ያካሂዳል፡፡
በዝግጅቱ ላይ ዶ/ር ዮናስ ባህረ ጥበብ፣ የሙዚቃ ባለሙያውና ተመራማሪ ሰርጸ ፍሬስብሃት፣ ገጣሚ ትእግስት ዓለሙ፣ አርቲስት አዜብ ወርቁ (የፕሮግራሙ አማካሪ)፣ ደራሲ በሀይሉ ገ/እግዚአብሄር፣ ገጣሚ ኤፍሬም ስዩምና ገጣሚ ታደለ ሲሳይ ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ ታውቋል፡፡