Saturday, 09 June 2018 12:10

“ኢትዮጵያዊነትን የመመለስ ተጋድሎ” ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)


     “ኢትዮጵያዊነትን የመመለስ ተጋድሎ” የተሰኘውና በቅርቡ ከ6 ዓመታት የእስር ቆይታ በኋላ የተፈታው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ መፅሐፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡
መፅሐፉ በዋናነት የረዥም ዘመን አኩሪ ታሪክ ያላት አገራችን ሲውሰበሰቡ በመጡና በመጨረሻም ግልፅ አደጋ ሆነው በተጋረጡባት ሁነቶች ምንነት፣ በሂደቱ ውስጥ የነበሩት ስልታዊ ሸፍጦችና የተዋናዮቹ ማንነት የተገለፀባቸው አይነተኛ መንገዶች ከዝርዝር መፍትሄዎቻቸው ጋር ቀርቦበታል፡፡
መፅሐፉ በተጨማሪም ከሃያ ዓመታት በላይ ከታሰሩ አንስቶ ህይወታቸውን በየእስር ቤቱ ስላሳለፉ ኢትዮጵያውያን ወደ ኋላ ከ40 ዓመት በላይ በመመለስ ይዘክራል ተብሏል፡፡ መፅሐፉ በ120 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 1495 times