በተማሪ ቅርፅ የተሰራው ሃውልት መታሰቢያነቱ ለመምህራን ነው ተብሏል፡፡ ሃውልቱን ቀድሞ የአሜሪካ ትምህርት ቤት ይባል የነበረው ኢንተርናሽናል ኮሙኒቲ ስኩል ያሰራው ሲሆን ተማሪዎቹ የሐውልቱን አረንጓዴ መስክ እንደሚንከባከቡ ታውቋል፡፡ የዲፕሎማቲክ መናኻሪያ የሆነችው አዲስ አበባ ማደግ የትምህርት ቤቱም ማደግ ነው ያሉት አምባሳደር ቡዝ፤ ሀገራቸው ለኢትዮጵያ ትምህርት እድገት ባለፉት ሦስት ዓመታት 80 ሚሊዮን ዶላር ማበርከቷን አስታውሰዋል፡፡