Saturday, 07 July 2018 11:56

“በትዝታ” የግጥም መድበል ሰኞ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በሚችጋን ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ መኩሪያ “በትዝታ” የተሰኘ የግጥም መድበል የፊታችን ሰኞ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር ይመረቃል፡፡
በሥነ ስርዓቱ የብሔራዊ ቴአትር ዋና ዳይሬክተር ረ/ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ፤ በመፅሐፉ ላይ ዳሰሳ የሚያቀርቡ ሲሆን ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ፣ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደና አርቲስት ፍቃዱ ከበደ ወግና ዲስኩር እንደሚያቀርቡ የፕሮግራሙ አዘጋጅ ምስክር ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን አስታውቋል፡፡
በተጨማሪም ገጣሚዎቹ ምስራቅ ተረፈ፣ ደምሰው መርሻና ዶ/ር ብርሃኑ መኩሪያ የግጥም ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡና ዝግጅቱን መሶብ ባህላዊ ባንድ እንደሚያጅበው ታውቋል፡፡

Read 4620 times