Saturday, 14 July 2018 11:48

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ዛሬ ከሃረሚያ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ይቀበላሉ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)


     የአማራ ክልል ርዕሠ መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ዛሬ ከሃረሚያ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት እንደሚሠጣቸው የታወቀ ሲሆን ከሳምንት በፊት የኦሮሚያ ክልል ርዕሠ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሣ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተቀብለዋል፡፡
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የክብር ዶክትሬቱ የሚሠጣቸው በክልላቸው ላሣዩት የአመራር ጥበብ እውቅና ከመስጠት አንፃር መሆኑን ምንጮች ለአዲስ አድማስ የጠቆሙ ሲሆን ሃረማያ ዩኒቨርሲቲ ከተቋቋመ ጀምሮ የክብር ዶክትሬት የሠጣቸው ሶስተኛው ሰው ይሆናሉ ተብሏል፡፡
ከአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጋር የመጀመሪያው የኦሮሚኛ ቋንቋ ጋዜጠኛ የሆኑት እና የተለያዩ የኦሮሚኛ ስነ ጥበባዊ ስራዎችን ያበረከቱት አርቲስት መሃመድ አህመድ ቆጴም የክብር ዶክትሬት እንደሚሰጣቸው ታውቋል፡፡
ሃረሚያ ዩኒቨርሲቲ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ የክብር ዶክትሬት የሠጠው ለሁለት ግለሠቦች ብቻ መሆኑ የታወቀ ሲሆን እነሡም የጅቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌ እና ታዋቂው ሳይንቲስት ፕሮፌሠር ኢጄታ ገቢሣ ናቸው፡፡
ሃረሚያ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው እለት 7 ሺህ 900 ተማሪዎችን በተለያዩ መርሃ ግብሮች እንደሚያስመርቅ ታውቋል፡፡
በሌላ በኩል ሠኔ 30 ቀን 2010 ዓ.ም የጅማ ዩኒቨርሲቲ በኦሮሚያ ክልል ለሠጡት በሣል አመራር ለክልሉ ፕሬዚዳንት ለማ መገርሣ የክብር ዶክተሬት ሰጥቷቸዋል፡፡

Read 3640 times