Print this page
Saturday, 21 July 2018 13:18

20 ሚ. ብር የፈጀ የባህል አዳራሽ ሥራ ይጀምራል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 ካፒታል ሆቴልና ስፓ በአገራችን የመጀመሪያ ነው የተባለለትን ባለ 5 ኮከብ ሆቴል ውስጥ የተገነባ ትልቅ የባህል አዳራሽ ዛሬ ከረፋዱ 4፡30 ጀምሮ ያስመርቃል፡፡ 20 ሚ. ብር የወጣበት እንደሆነ የተነገረለት የባህል አዳራሹ፤ የኢትዮጵያን ድንቅ ባህል፣ ሙዚቃና ውዝዋዜ፣ የአገሪቱን እሴቶችና ምግቦች ለመላው ዓለም ለማስተዋወቅ ታልሞ መገንባቱን የሆቴሉ ባለቤትና ስራ አስፈፃሚ አቶ የማነ ገ/ሥላሴ ገልፀዋል፡፡
የባህል አዳራሹ የአገራችን የኪነ ህንፃ ጠበብት እውቀታቸውን እንዳፈሰሱበት የተነገረ ሲሆን ሙቀትና ቅዝቃዜውን የሚያመጣጥን ቴክኖሎጂ፣ ድንገተኛ አደጋ ቢፈጠር የቅድመ ጥንቃቄ ጠቋሚ መሳሪያና ለጆሮ ማራኪ የሆነ ሳውንድ ሲስተም የተገጠመለት፣ ነገር ግን ሙሉ ኢትዮጵያዊ ገፅታን የተላበሰና የአገሪቱ የባህል አምባሳደር መሆን የሚችል ማዕከል ነው ተብሏል፡፡ በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅትና ከሚመለከታቸው ተቋማት የተወከሉ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Read 4168 times