ሚዩዚክ ሜይዴይ ከኢትዮጵስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር፣ ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ታሪክ ላይ ተመስርቶ በተሰራው “HIM Haile Selassie The Lion of Judha” የተሰኘ ዘጋቢ ፊልም ላይ በብሔራዊ ቤተ መፃሕፍትና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ አዳራሽ ውይይት ያካሂዳል፡፡
ለውይይቱ መነሻ ሃሳብ የሚያቀርቡት አቶ አዳሙ ብርሃኑ ሲሆኑ መድረኩ የሚመራው በታሪክ ባለሙያውና መምህሩ ሰለሞን ተሰማ ጂ. እንደሆነ ታውቋል፡፡ ፍላጎት ያለው በውይይቱ ላይ እንዲሳተፍ ሚዩዚክ ሜይዴይ ጋብዟል፡፡