Saturday, 28 July 2018 16:11

በ“ሕያው ስሜት” የስዕል ትርኢት ላይ ነገ ውይይት ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 ከአንድ ወር በፊት በጋለሪያ ቶሞካ በተከፈተው 26ኛው ዙር “ሕያው ስሜት” የተሰኘና በሰዓሊ ዳንኤል አስፋው 35 የስዕል ስራዎች ላይ ነገ ከረፋዱ 4፡00 ጀምሮ ውይይት ይካሄዳል፡፡
በውይይቱ ላይ በርካታ ሰዓሊያን፣ የስዕል አፍቃሪያንና ሰዓሊው የሚገኙ ሲሆን ሰዓሊ እሸቱ ጥሩነህ ለውይይት የሚሆን የመነሻ ሀሳብ እንደሚያቀርብና ከታዳሚ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሰዓሊው ምላሽ እንደሚሰጥ ጋለሪያ ቶሞካ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

Read 4510 times