Saturday, 04 August 2018 11:05

E- Learning- ትምህርትን በኢንተርኔት….

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(2 votes)

   በአለም አቀፍ ዙሪያ እንዲሁም በኢትዮጵያም በአንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች ትምህርትን በሶፍትዌር አማካኝነት መስጠት የተጀመረ አሰራር ነው፡፡ ትምህርት በትምህርት ቤቶች ፤ትምህርትን በተልእኮ ከመሳሰሉት የትምህርት አሰጣጥ ዘዴዎች በተጨማሪ ትምህርትን በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ በመላላክ መቅሰም የሚያስችለው ዘዴ በአለም ላይ ከተጀመረ ትንሽ የቆየ ሲሆን በአገራ ችንም በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በስራ ላይ መሆኑ እየታየ ነው፡፡ የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ከአሜሪካው የጽንስና ማህጸን ሕክምና ኮሌጅ ጋር በመቀናጀት ከሚሰራቸው ስራዎች አንዱ የሆነው የዚህ የትምህርትን በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ለጽንስና ማህጸን ሕክምና ባለሙያዎች ምቹ የማድረግ ሁኔታ ከመጀመሩ አስቀድሞ ስራውን እንዲከናወን ለሚያደርጉ ባለሙያዎች የስልጠና እድል ተሰጥቶአል። ይህንኑ በሚመለከት ከአሜሪካ ከመጡት እንግዳ በተጨማሪ ከጤናጥበቃ ሚኒስቴር ፤ከቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ከመጡ ባለሙያዎች ሀሳብ ወስደን እነሆ ለንባብ ብለናል፡፡
ዶ/ር ብርሀኑ ታደሰ በኢትዮጵያ የማህጸን ጽንስ ሐኪሞች ማህበር እና በአሜሪካው የጽንስና ማህጸን ኮሌጅ መካከል ባለው የፕሮጀክት አተገባበር የፕሮግራም ዳይሬክተር ናቸው፡፡ እሳቸው እንደሚሉት ከአሜሪካ ወደኢትዮጵያ ስልጠና ለመስጠት የመጣው ቡድን E Learning የተባ ለውን ትምህርት በምን አይነት መንገድ እውቀቱን ለማግኘት ለሚፈልጉ ባለሙያዎች ማዳረስ ይቻላል የሚለውን በአገር ውስጥ ላሉና ፕሮግራሙን ሊመሩ ይችላሉ ለተባሉት የጽንስና ማህ ጸን ሕክምና ባለሙያዎች እንዲ ሁም ከኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሚመለከታቸውን ባለ ሙያዎች ለማሰልጠን ነው፡፡ እስከአሁን የተለመደው ትምህርት በሴሚናር መልክ ወይንም ፊት ለፊት አስተማሪውና ተማሪው ተገናኝተው ገለጻ በመስጠት የሚካሄድ ሲሆን ይህ ግን አስተማ ሪዎቹና ተማሪዎቹ በቀጥታ ሳይገናኙ በኤሌክ ትሮኒክ ማለትም በቪድዮ ወይንም በኢንተርኔት አማካኝነት ትምህርቶቹን በማስተላለፍ እንዲማሩ የሚደረግበት መንገድ ነው፡፡ ስለዚህም ያንን ስልጠና እንዴት ነው ማዘጋጀት የሚቻለው ? ከስልጠናው ጋር በተያያዘም ሌሎች አስፈላጊ ነገሮች እንዴት ነው የሚመሩት የሚለውን በተመለከተ በአሜሪካን አገር ይህንን ተመሳሳይ ትምህርት የሚሰጡ ባለሙያዎች ወደኢትዮጵያ እንዲመጡ ተደርጎአል፡፡
ዶ/ር ብርሀኑ አክለው እንደገለጹትም ካለው የቴክኖሎጂ መስፋፋት ጋር በተያያዘ ይህ የትም ህርት አሰጣጥ ዘዴ በአለም ላይ በጣም እየተስፋፋ የመጣ ሲሆን የሚገርመው ግን ይበልጥ በማገልገል ላይ ያለው በማደግ ላይ ያሉ አገሮችን ነው፡፡ የዚህም ምክንያቱ ሁልጊዜ አስተማሪ ዎችን በየቦታው ወስዶ ሐኪሞችን ማስተማር አይመችም፡፡ነገር ግን ይህ በቴክኖሎጂ የታገዘ የትምህርት አሰጣጥ ዘዴ ቢለመድና ክህሎቱ ቢዳብር የጤና ባለሙያዎች የትም አካባቢ ማለ ትም እርቀት ካለው ስፍራ ወይንም ገጠር እንኩዋን ቢሆኑ በቀላሉ የሚሰራጨውን ትምህርት በኢንተርኔት አማካኘነት ሊያገኙት ይችላሉ፡፡  በዚህም ምክንያት ጊዜና ገንዘብ በማይፈልግ ሁኔታ ባሉበት ቦታ ስራቸውን እየሰሩ በምትኖራቸው ትርፍ ጊዜ በመጠቀም ዘመናዊ የሆነ የትምህርት እድገት በቶሎ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፡፡
ይህንን አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ የተወሰኑ አደረጃጀቶችን እንደሚጠይቅ ባለሙያው አክለው ተናግረዋል፡፡ ይህም ትምህርቱን መስጠት ወይንም እንዲቀዳ ማድረግ እና ተቀድቶም በፕሮግ ራም እንዲካተት ማድረግ የሚችል ባለሙያ ማግኘት አንዱ ሲሆን በሌላው በኩል ደግሞ ቴክኖ ሎጂውን ወይንም ኢንተርኔትን በመጠቀም በሶፍትዌር አማካኝነት ማግኘት ነው፡፡ ይህ ካልተ ቻለ ደግሞ የተቀዳውን ትምህ ርት በፍላሽ ወይንም በሲዲ ወስዶ ለማንበብ ወይንም እውቀትን ለማዳበር በሚፈለግበት ቦታ ሁሉ ማሰራጨት ይቻላል፡፡ስለዚህ የሚጠይቀው ነገር በመጀመሪያ የራስን ፍላጎት ሲሆን ከዚህ ውጪ ብዙ ወጪ የማይነካ በአነሰ ወጪ በጣም ብዙ ሰዎችን ለማስተማር የሚረዳ ነው፡፡ ይህንን ስራ አገር ውስጥ ባሉ ባለሙያዎች እንዲተገበር እንደ ኢሶግ ባለ ተቋም የቴክኒክ እገዛ ማድረግ ይችላል፡፡ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርም ይህ ትምህርት ለማን በምን በኩል መሰጠት አለበት የሚለውን ይህን ትምህርት በመውሰድ ከፈቃድ እድሳትና በሙያው ላይ ከመቀጠል አንጻር ጭምር  አብሮ በማስ ተሳሰር አቅሙ ካላቸው እንደኢሶግ ካሉ የሙያ ማህበራት ጋር በጋራ በመሆን ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ ይችላል፡፡ ይህ ከተደረገ በአገሪቱ አዲስ እና ዘመናዊ ትምህርትን እንዲሁም አሰራርን በማስፈን ተገልጋዩን ሕብረተሰብ በተሟላ እውቀት በዘመናዊ መንገድ ጥራትና ብቃት ባለው መንገድ ማገልገል  የሚችሉ ባለሙ ያዎችን ለማፍራት የሚያስችል ስለሆነ የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ ድጋፍና አስተዋጽኦ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል ዶ/ር ብርሀኑ ከበደ፡፡
አቶ ሳላዲን ሰይድ በኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በሰው ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት የተከ ታታይ የሙያ ማሻሻያና ሙያ ማጎልበቻ ክፍል አስተባባሪ በስልጠናው ላይ ተሳትፈዋል፡፡ እሳቸው እንደገለጹትም የሚሰሩበት ክፍል የተከታታይ የሙያ ማጎልበቻ እና ማሻሻያ በሚል ስራውን ከጀመረ የተወሰኑ አመታት የሆነው ሲሆን ከኢትዮጵያ የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር ጋር በመሆን በዘልማድ የሚሰጡትን ስልጠናዎች ማለትም አስተማሪዎች ፊት ለፊት ቆመው የሚሰጡትን በምን መንገድ በተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ፤ ስልጠናውን ለሚፈልጉ ሁሉ ማዳረስ ይቻላል? አዲስ ለሚመረቁ ባለሙያዎችስ በምን መንገድ አጫጭር ስልጠናዎችን ማዘጋጀት ይቻላል የሚለውን እውቀት ለማግኘት በስልጠናው ተሳትፈናል፡፡ ከዚህም የምናገኘው እውቀት በስራ ላይ ላሉ ባለሙያዎች ስልጠናዎችን እንዴት ማዘጋጀት ይቻላል? ከአሁን ቀደም የሚሰጡ ስልጠናዎችንስ በምን መልኩ በቴክኖሎጂ አማካኝነት ተደራሽ ማድረግ ይቻላል?  በፍላሽ ወይንም በቪድዮ እና በሶፍትዌር አማካኝነት ትምህርቱን የሚፈልግ ማንኛውም ባለሙያ በራሱ ሰአት ምንም አይነት ግዴታ በሌለበት ሁኔታ በቤት ውስጥ ወይንም በስራ ላይ እያለ በሚኖረው ክፍት ጊዜ አለዚያም በመዝናኛ ቦታው አረፍ ብሎ እጁ ላይ ባሉት መሳሪያዎች አማካኝነት ማለትም በፍላሽ ወይንም በኢንተርኔት አማካኝነት እውቀቱን ለማሻሻል እንዲችል ለማድረግ የሚያስችል ነው፡፡ ይህ አሰራርም ስልጠናውን የተከታተለው ሰው ምን ያህል እንደተጠቀመ ከተዘረጋው የአሰራር ዘዴ ለማወቅ ይቻላል፡፡ ይህ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚያደርገው እገዛ ምንድነው ሲባል ….
ከተደራሽነት አንጻር በጣም በአጭር ጊዜ በተመሳሳይ ሰአት እርቀት ሳያግደው ካለምንም ጊዜ ማባከንና የገንዘብ ወጪ በብዙ ቦታዎች ተሰማርተው የሚገኙ ባለሙያዎችን ማሳ ተፍ ያስችላል፡፡
ከወጪም አንጻር በተለይም ከአገር ውስጥም ይሁን ከውጪ ሀገር ትምህርቱን በአካል ፊት ለፊት ቀርበው ለሚሰጡ ባለሙያዎች እንዲሁም ሰልጣኞቹ ከየአሉበት ቦታ ወደ ስልጠናው ማእከል ለመምጣት ሲሉ የሚያወጡትን የትራንስፖርት ወጪ ለመተካት ሲባል የሚኖረውን የገንዘብ ጫና ይቀንሳል፡፡ በግንባር ለመሰልጠን የሚመጡ ሰልጣኞች በሚኖራቸው ቆይታ የአበል፤ የእለት የሆቴል ምግብ ፤የአዳራሽ ኪራይ የመሳሰሉትን ወጪዎች ሁሉ ይቀንሳል፡፡
ባለሙያዎቹ ካሉበት አካባቢ ስልጠናውን ለመውሰድ ሲሉ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ቀናትን ስለሚወስድባቸው ለሕክምና የሚመጡ ተገልጋዮች ሐኪሙን እንዳያገኙ ምክንያት ይሆናል፡፡ እንዲሁም ያ ሐኪም በቦታው ስለሌለ ስራውን ደርቦ በሚሰራው ሐኪም ላይ ጫና ሊፈጠር ስለሚችል ክፍተት ሊኖር ይችላል፡፡…ወዘተ
ማንኛውም ባለሙያ ከዩኒቨርሲቲ ተምሮ ከወጣ በሁዋላ እስከዘላለሙ ትምህርት በቃው፤ማንበብ ማቆም አለበት ወይንም ስልጠና አያስፈልገውም እውቀትን ወይንም ክህሎትን ማሳደግ ማቆም አለበት የሚያሰኝ ነገር የለም፡፡ በተለይም በጤናው ሴክተር ላይ የሚሰማሩ ባለሙያዎች ሁኔታ ከሌሎች የሚለይበት ምክንያት ሳይንስ ተቀያያሪ በመሆኑና የህክምና መስጫ ዘዴው የሚለወጥ ወይንም የሚያድግ ፤ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች የሚመጡ መሆን እንዲሁም አዳዲስ ጥናቶች ለህብረተሰቡ በየጊዜው ይፋ መሆናቸው ነው፡፡ አንድ ሰው ከዩኒቨርስቲ ከተመረቀ ከአምስት አመት በሁዋላ እውቀት የተሸረሸረ የሚሄድ በመሆኑ በንባብም ይሁን በስልጠና ሁልጊዜ እራ ሱን ከአዲስ አሰራር ጋር እንዲያገናኝ እና እውቀቱን እንዲያዳብር ይገደዳል፡፡ የዚህም ምክ ንያት ስራው የሚሰራው ከሰው ሕይወት ጋር በተያያዘ በመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄን ማድረግ ይጠይ ቃል፡፡ ስለዚህም አንድ የህክምና ባለሙያ በአምስት አመት ውስጥ 150/አንድ መቶ ሀምሳ ሰአት፤ በአንድ አመት ውስጥ ደግሞ 30/ሰላሳ ሰአት የሙያ ማዳበሪያ ስልጠና መውሰድ አለበት ተብሎ እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2013/የወጣ መመሪያ አለ፡፡ በእርግጥ መሟላት ያለባቸው ነገሮች ስላሉ ሙሉ በሙሉ ወደስራው ስላልተገባ በአሁኑ ወቅት አንድ ባለሙያ ጤነኛ መሆ ኑና ከድርጅቱ የስራ ልምዱን ካቀረበ የሙያ ፈቃዱ ይታደሳል፡፡ ነገር ግን እንዲሆን የሚፈለ ገው ህብረተሰቡን በአዳዲስ ቴክኖሎጂ ውጤቶችና የህክምና አሰራሮች ማገልገል እን ዲችል እውቀቱን በየጊዜው በስልጠና እንዲያግዝ እና እውቀቱን ማበልጸግ እንዲችል ማድረግ ነው፡፡ ይህ የ E - Learning  ስልጠና ወደ ተግባር ከተገባበት “ እርቀትና ጊዜ ሳገድበው በቀላሉ ባለሙያውን ለማግኘትና ለማሰልጠን ምቹ መሆኑ አያጠያይቅም፡፡

Read 2011 times